Get Mystery Box with random crypto!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ housinginaddisababa — Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች H
የቴሌግራም ቻናል አርማ housinginaddisababa — Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች
የሰርጥ አድራሻ: @housinginaddisababa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.64K
የሰርጥ መግለጫ

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates.

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 124

2022-08-30 03:30:38 #የአከራይ ተከራይ "ደንቡ" ስግብግብ ተከራዮችን ጭምር ለመቆጣጠር ገደብ ሊበጅለት በተገባ ነበር!

ዛሬ ለሥራ ጉዳይ ወደ አንድ ወረዳ ፅ/ቤት ጎራ ብዬ ነበር። ሰሞኑን ለአዲሱ ዓመት በዓል ብሎም ለ6 ወራት ያህል እዚሁ አዲስአበባ ለመክረም ከአሜሪካ የተመለሱ ባልና ሚስት ብሶታቸውን ለሚመለከታቸው እየገለፁ አገኘኋቸው። ንትርኩ ሲጠናቀቅ ቀረብ ብዬ ችግራቸውን ጠየቅኳቸው። ምናልባት የገጠማቸው ችግር የሌሎችም ዲያስፖራዎች ይሆናል በሚል ገፄ ላይ ላካፍላችሁ ወሰንኩ... ነገሩ እንደዚህ ነው፦

ዲያስፖራዎቹ ባልና ሚስት ከሁለት ዓመታት በፊት አዲስአበባ የነበራቸውን ቤት አከራይተው ነበር ወደ አሜሪካ የሄዱት።ለዓመት በዓል ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለሱና በቀጣይነትም ለስድስት ወራት አዲስአበባ ለመቆየት ዕቅድ ስለያዙ ተከራዮቹ ቤታቸውን በመልቀቅ ሌላ መፍትሔ እንዲያፈላልጉ ከአራት ወራት በፊት ከወደ አሜሪካ ደውለው ሲያሳውቋቸው... "አዳነች አቤቤ ቤቱን እንዳትለቁ የሚል ደንብ ስለወጣች ፈፅሞ አንለቅም" በማለት በስልክ ምላሻቸውን ሰጡ። ዲያስፖራዎቹ ምናልባት እኛ በአካል ስንመጣ ይለቃሉ በሚል ግምት በአካል አዲስአበባ ድረስ ቢመጡም ተከራዮቹ "ወይ ፍንክች የአባ ቢላ ልጅ" ሆኑባቸው። እናም አሁን ከውጭ ተመላሾቹ ባልና ሚስት ቤት አልባ ሆነው ከሆቴል ሆቴል እየተንከራተቱ ይገኛሉ። ተከራይ የወጣውን አዋጅ ተገን አድርጎ በሌላ ሰው ንብረት ደረቱን ነፍቶ ለቀጣይ 6 ወራትም እዚያው ለመኖር ወስኗል። ከ6 ወራት በኋላ ደግሞ ደንቡ ዳግም ሊራዘምም ይችላል።

የዲያስፖራዎቹ ቤት ተከራይ በቂ ገቢና ሁለት መኪናዎች ያሉት(ለራሱና ለሚስቱ) እንደሆነ ዲያስፖራዎቹ ነግረውኛል። ኧረ ምን ይኼ ብቻ? ተከራይ የራሱን ቤት ሰርቶ ጨርሶ በውድ ዋጋ አከራይቶ ነው በዲያስፖራዎቹ ቤት ከሁለት ዓመታት በፊት በነበረው የኪራይ ዋጋ ተመን እየኖረ ያለው። ለማንኛውም የወረዳው ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ከፈለጋችሁ ፍርድ ቤት ሂዱና ተከራከሩ ብሎ ሸኝቶአቸዋል። እንግዲህ በተመሳሳይ መልኩ ለዓመት በዓል ከውጭ የሚገቡ ዲያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት የሚመለሱት በዓሉን በደስታ ለማክበር ሳይሆን ፍርድ ቤት ለመመላለስ ነው። So sad!

ኑሮ ውድነቱን ሰበብ አድርገው ማህበረሰቡን ሆን ብለው በሚጎዱ አከራዮች ላይ መመሪያው መውጣቱ መልካም ነው። ሆኖም መመሪያውን ተገን አድርገው የራሳቸውን ቤት በውድ ዋጋ አከራይተው በሌላ ሰው ቤት በከረመ የኪራይ ተመን እየኖሩ ዓለማቸውን እየቀጩ ለመኖር በቋመጡት ላይ ግን መቋጫ መበጀት ነበረበት።

መንግስት የዲያስፖራ አባላት ለአዲሱ ዓመት ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡ ጥሪ ሲያደርግ ይደመጣል፣ ከመጡ በኋላ ግን ቤት እያላቸው በቤታቸው እንዳይኖሩ ግራ-ገብና ገደብ አልባ ደንብ ያወጣባቸዋል። በአሁኑ ወቅት በአከራይና በጋጠ-ወጥ ስግብግብ ተከራይ መካከል ያለውን እንቶ ፋንቶ መታዘብ የፈለገ ወደ ወረዳዎች ሰላምና ፀጥታ ቢሮዎች ብቅ ብሎ ይመልከት። ይሰመርልኝ...የልጥፉ መልዕክት የሚመለከተው የራሳቸውን ቤት ጨርሰው ሰርተው በውድ ዋጋ አከራይተው ተከራይተው የሚኖሩበትን ቤት ለመልቀቅ ፈቃደኛ ያልሆኑ ተከራዮችን ብቻ ነው። መንግስትም እኮ አንድ ሰው የራሱ ቤት ካለው ቀድሞ ተከራይቶ ይኖርበት የነበረውን የመንግስት/የቀበሌ ቤት እንዲለቅ ያስገድዳል። ግለሰቦች ግን በገዛ ንብረታቸው እንደዚህ ዓይነት ውሳኔ እንዳይወስኑ በ"ደንብ" ስም ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።

ስለዚህም የሚመለከታችሁ የአዲስአበባ ኃላፊዎች ደንቡን ወይ አሻሽሉት ካልሆነም አስቀድሞ አዲስአበባ ቤት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት መጥተው በዘገምተኛ የፍርድ ቤት ሂደት እንዳይጉላሉ እዚያው ውጭ ሀገር እያሉ የደንቡ የጊዜ ገደብ እስኪያበቃ ወደ ሀገራቸው እንዳያቀኑ እዚያ እያሉ አሳውቋቸው።

Getahun Heramo
13.4K views00:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:39:56 በቆቦ ከተማ ንጹሃን መግደላቸው ተሰማ!
ሕወሓት ወደድርድር እንዲመጣ ተጠየቀ
በዓባይ ወንዝ ጎርፍ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 100 ደረሰ
የኢትዮጵያ አየር ኃይል በላቀ ዝግጁነት ላይ መሆኑ ተገለጸ።
373 የግል ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች እርምጃ ተወሰደባቸው ተባለ።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት የሙከራ ስራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡
ቱርክና ፈረንሳይ ውጥረት ውስጥ መግባታቸው ተሰማ!
የአየር መንገዱ አብራሪዎች በረራ ክፍል ውስጥ ከተደባደቡ በኋላ ከሥራ ታገዱ



16.0K views15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:11:35 የዩኒቨርሲቲ መምህራን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ቅሬታ እንደተሰማቸው ተናገሩ!
የመከላከያ ሰራዊት ወደ መቀሌ እያመራ መሆኑ ተገለጸ።
በአንዳድ የአማራ ክልል አካባቢዎች የሰዓት ዕላፊ ገደብ እየተጣለ ነው!
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከቅጥር ግቢያቸው እየወጡ ነው!
ታዬ አጽቀስላሴ ለተመድ የህወሓትን ድርጊት አስረዱ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አልጀርስ ገቡ!
የአልቃዒዳው መሪ አል-ዛዋሂሪ በአሜሪካ እንዲገደል ፓኪስታን የአየር ክልሏን ፈቅዳለች ሲል ታሊባን ከሰሰ!
በከፍተኛ የሙቀት መጠን ውስጥ ያለችው ቻይና ከደመና ዝናብ ለማዝነብ ድሮን አሰማራች!



17.4K views07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 07:58:46

17.1K views04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:26:21 ህወሓት ለዳግም ጦርነቱን የሚያስፈልገውን ሀብት ከየት አገኘ የሚል ጥያቄ ተነሳበት!
የለሚኩራ  ክፍለከተማ መሬት አስተዳደር ታሽጓል፤በሙስናና ህዝብን በማማረር የተጠረጠሩ ተለቅመው ታስረዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ!
የደብረፅዮን ደብዳቤ እያነጋገረ ነው!
የህወሀት አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ሥር ዋለ!
ጋዜጠኛና አክቲቪስት ሄርሜላ ሀረጋዊ የአለም የጤና ድርጅትን በአሽብር ለተፈረጀ ቡድን መሳሪያነት መጠቀም ወንጀል ነው አለች።
የኢትዮጵያ ሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጦርነቱ ያሳስበኛል አለ!
የሽንት ቤት አይነ-ምድርን ወደ ገንዘብ የቀየረው ሳይንቲስ እየተደነቀ ነው!



18.4K views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 16:59:08 የተመድ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር በኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸው ግጭት እንዲቆም ተማፀኑ።
በሲዳማ ክልል አዲስ የዞን አደረጃጀት ፀደቀ።
ኢትዮጵያ ያገኘችው የጋዝ ክምችት የመደራደር አቅሟን እንደሚያሳድግ ተገለጸ
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ እና ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬታቸውን ተቀበሉ!
የእምቦጭ አረምን የስራ እድል መፍጠሪያ ለማድረግ እንደሚያግዙ በኢትዮጵያ የኢንዶኔዥያ አምባሳደር አስታወቁ
ሩሲያ በሃንጋሪ የኒውክሌር ማብላያ ጣቢያዎችን ልትገነባ ነው!
በሀዘን ላይ የምትገኘው አንጎላ በተካሄደ ሀገር እቀፍ ምርጫ ገዢው ፓርቲ አሸነፈ!



19.0K views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 10:25:31 ጦርነቱ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የነዋሪዎች ሥጋት ማየሉ ተሰማ!
ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ለኬንያ ለመሸጥ የሚያስችል ውል ማሰሯን ገለጸች!
የወሰን ማካለሉ እንዲቆም ተጠየቀ!
በኮንዶሚኒየም ማጭበርበር ተጠርጥረው የታሰሩት በዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ደቡብ ሱዳን ሊያቀኑ ነው!
ለዘመዶቼ ገንዘብ መላክ አልቻልኩም" ሲሉ ዶ/ር ቴድሮስ አማረሩ።
በጎርፍ አደጋ ጉዳት ከ33 ሚ ሰዎች በላይ ደረሰባቸው!



18.7K views07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 05:37:21 የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም?

በአንድ ወቅት አንድ የማውቀው ሰው የተከራየው የንግድ ቤት አከራዮች ኑሮ እየተወደደ ስለሆነ ትንሽ ብር እንዲጨምርላቸው ጠየቁት። እሱ ግን ውላችን አምስት አመት ስለሆነ አልጨምርም አለ።ሰዎቹ አምስት አመት ሲሞላ ጠብቀው ውጣ አሉት።ቤቱ ስራ ስለነበረው እጥፍ ልጨምር ቢልም ቤታችንን እንድትለቅ ነው የምንፈልገው አሉት።ቢለምን ቢያስለምን እምቢ አሉት። ቀጥሎ አይኑ እያየ እሱ ከሰጣቸው ዋጋ ባነሰ ብር ለሌላ ሰው አከራዩት።

እዚህ የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም የሚለውን የግለሰብን የንብረት ባለቤትነት መብት የሚጥስ አዋጅ ደግፈህ ጮቤ የረገጥክ ከትንሽ ግዜ በኃላ ባለቤቱ ያገኝሀል። አንድ ሰው ጥሮ ግሮ የሰራውን ቤት ለማን ማከራየት እንዳለበት፣ በስንት ማከራየት እንዳለበት የሚወስነው እሱ እንጂ መንግስት። አዛኝ ከሆነች በራሷ ገንዘብ ቤት ሰርታ ማከራየት ነው።

ሲጀመር የቤት ኪራይ እየጨመረ ያለው አከራዩ አይደለም።እንደማንኛውም እቃ የቤት ኪራይ ዋጋ እና የወለድ ምጣኔም መንግስት አትሞ ከረጨው ብር ጋር እራሳቸውን adjust እያደረጉ ስለሆነ ነው። መንግስት የመብራት ታሪፍ በእጥፍ ልጨምር ነው ከሚለው ዜና ቀጥሎ ግለሰቦች የቤት ኪራይ መጨመር አይችሉም የሚባልባት ሀገር በጣም ታስቃለች። የቤት ኪራይን ጨምሮ የሁሉንም እቃ ዋጋ ጣርያ አስነክቶ የይስሙላ "የቤት ኪራይ አትጨምሩ" የሚል አዋጅ ያወጣውን መንግስት ማመስገን ችግሩን አይፈታውም።

Mekoya Kebede
18.7K views02:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 23:39:52 ፍርድ ቤቱ ከኮንዶሚኒየም ዕጣ ማጭበርበር ወንጀል ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ 5 የሶፍትዌር ባለሙያዎች በ60 ሺሕ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ፈቀደ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ከኮንዶሚኒየም ዕጣ ማጭበርበር ወንጀል ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ 5 የሶፍትዌር ባለሙያዎችን በ60 ሺሕ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ፈቅዷል።

ዋስትና የተፈቀደላቸው ተጠርጣሪዎች የቤቶች ልማት ዳታ ቤዝ ቡድን መሪ ስመኘው አባተ እና የሶፍትዌር ባለሙያዎች ሀብታሙ ከበደ፣ ዮሴፍ ሙላት፣ ጌታቸው በሪሁን እንዲሁም ቃሲም ከድር ናቸው።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች በዋስ ቢወጡ እንደማይቃወም ፖሊስ ለችሎቱ አስተያየት መስጠቱን ተከትሎ ዋስትና ተፈቅዶላቸዋል።

ቀሪዎቹ ማለትም፤ የአ/አ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና አይሲቲ ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አብርሐም ሰርሞሌ፣ የቤቶች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ሚኪያስ ቶሌራ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አይሲቲ ሀላፊ ኩምሳ ቶላ በሚመለከት ደግሞ በመርማሪ ፖሊስ በተገለጸው ከተለያዩ ተቋማት የሚሰበሰቡ ማስረጃዎች እና የቀሪ ሥራ በመኖሩ ችሎቱ አሳማኝ ምክንያት ነው ሲል የ12 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መፍቀዱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።

በአጠቃላይ ተጠርጣሪዎቹ ከ14ኛው ዙር 20/80 እና የ3ኛ ዙር የ40/60 የአ/አ ከተማ ከኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ላይ ያልቆጠቡና በወቅቱ ያልተመዘገቡ ግለሰቦችን ያለአግባብ በዕጣው እንዲያካትቱ አድርገዋል ተብለው በቁጥጥር ሥር ውለው ከአንድ ወር በላይ በእስር ላይ የነበሩ ናቸው።

በሌሎች መዝገቦች በተለያዩ ቀናት ከዚህ በፊት የቀረቡ ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱን ጨምሮ 7 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ግን እንደቀጠለ ነው።

በተለይም ለኮዶሚኒዬም ዕጣ ጉቦ ተቀብለው 5 ሰዎችን በዕጣው እንዲካተቱና ቤት እንዲደርሳቸው አድርገዋል የተባሉ 3 የስፍትዌርና ዳታ ቤዝ ባለሙያዎች ባሳለፍነው ሳምንት በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛሉ።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች 1ኛ የአ/አ ቴክኒክና ሙያ ስልጠናና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሶፍትዌር ባለሙያ የነበረ አሚ አምባዬ የሚባል ሲሆን፤ 2ኛ ተጠርጣሪ የዳታ ቤዝ ሰራተኛ የነበረ ዮናስ ወ/ጊዮርጊስ እና 3ኛ የዳታ ቤዝ ሰራተኛ የሆነችው አብረኸት ልዑል ናቸው።

በተለይም 3ኛ ተጠርጣሪ አብረኸት ልዑል በበኩሏ "አንድ ሰው መጥቶ ገንዘብ እየተከፈለ የቤት ዕጣ መካተት ይቻላል ወይ ሲል ጠይቆኝ ነበር እኔ ደግሞ 2ኛ ተጠርጣሪን ዮናስን ስጠይቀው አዎ ገንዘብ ተከፍሎ የሚያካትት አለ አለኝ። ከዛ በኋላ ግለሰቡ የባንክ ሂሳቤ ላይ የሶስት ሰዎችን አጠቃላይ 850 ሺህ ብር ካስገባልኝ በኋላ ኹሉንም ገንዘብ ለ1ኛ ና ለ2ኛ ተጠርጣሪዎች በባንክ ሂሳባቸው አዛውሬላቸዋለው" ስትል ለፍርድ ቤቱ መግለጿን መዘገባችን ይታወሳል።
____
አዲስ ማለዳ
17.9K viewsedited  20:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 23:39:23
ፍርድ ቤቱ ከኮንዶሚኒየም ዕጣ ማጭበርበር ወንጀል ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ 5 የሶፍትዌር ባለሙያዎች በ60 ሺሕ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ፈቀደ
16.7K viewsedited  20:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ