Get Mystery Box with random crypto!

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የአገልግሎቶቹን ክፍያ በቴሌብር በኩል መፈጸም የሚያስች | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የአገልግሎቶቹን ክፍያ በቴሌብር በኩል መፈጸም የሚያስችል ስምምነት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ተፈራረመ

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የአገልግሎት ክፍያ ሥርዓቱን በማዘመን፤ የአገልግሎቶቹን ክፍያ በቴሌብር በኩል መፈጸም የሚያስችል ስምምነት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በዛሬው ዕለት ተፈራርሟል።

በዚህም መሠረት የኤጀንሲው ባለጉዳዮች ያለምንም ውጣ-ውረድ እና እንግልት የመኪና ሽያጭ ውል፣ የስጦታ፣ የውክልና፣ የብድር፣ የማህበር ምስረታ እና ቃለ ጉባኤ የመሳሰሉ ከ27 በላይ አገልግሎቶቹን ክፍያ በቴሌብር መፈጸም እንዲችሉ መደረጉ ተገልጿል፡፡

ባለጉዳዮች ኤጀንሲው የሚሰጣቸውን የክፍያ ማዘዣ ቁጥር በመጠቀም፤ በቴሌብር መተግበሪያ ወይም በአጭር ቁጥር (*127#) የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀላሉ መፈጸም እንደሚችሉም ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡
_
አዲስ ማለዳ