Get Mystery Box with random crypto!

80 የጋራ መኖርያ ቤቶች ለነዋሪዎች ተሰጡ በዛሬው እለት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

80 የጋራ መኖርያ ቤቶች ለነዋሪዎች ተሰጡ

በዛሬው እለት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የልቤ ፋና ትምህርት ቤት ሲገነቡ የቆዩትን ሁለት ህንፃ ጨምሮ በአጠቃላይ አራት ህንፃዎችና 80 የጋራ መኖርያ ቤቶች ተጠናቀው ተመርቁ።

ህንፃዎቹ በተገነቡበት ቦታ ላይ ለነበሩት ነዋሪዎችም እንደ ነበራቸው መኖሪያ ስፋትና መጠን በቤቶቹ በይፋ እጣ በማውጣት አስተላልፈዋል፡፡

እነዚህ ቤቶች ግንባታቸው ከተጀመረ በኋላ መሬቱን በሚፈልጉ ግለሰቦች ለ9 ወራት ያህል በፍርድ ቤት እግድ አስቁመው የነበረ ሲሆን፣ መስተዳድሩ በአጭር ጊዜ ቤቶቹን ገንብቶ በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ መተላፍ ችሏል፡፡

ቤቶቹን በተመጣጣን ዋጋ ገንብቶ ያጠናቀቀው ደግሞ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ምስጋና አቅርበዋል ፡፡