Get Mystery Box with random crypto!

'አፍሮ ባሮ ሜት' የተሰኘው የጥናትና ምርምር ተቋም፣ በፈረንጆች 2023 ከ10 ኢትዮጵያዊያን ስድስ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

"አፍሮ ባሮ ሜት" የተሰኘው የጥናትና ምርምር ተቋም፣ በፈረንጆች 2023 ከ10 ኢትዮጵያዊያን ስድስቱ በከፋ ወይም በመካከለኛ ድህነት ውስጥ ማለፋቸውን በጥናት ማረጋገጡን ገልጧል። ተቋሙ ከበፈረንጆች 2020 ጋር ሲነጻጸር፣ በከፋ ወይም መጠነኛ ድህነት ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በ7 በመቶ መጨመሩን አስታውቋል።በጥናቱ መሠረት፣ በ2023 የምጣኔ ሃብት ኹኔታው "በጣም መጥፎ" ወይም "መጥፎ" መኾኑን ለጥናቱ የገለጡ ኢትዮጵያዊያን 65 በመቶ ሲኾኑ፣ በ2020 ግን ቁጥሩ 45 በመቶ ብቻ እንደነበር ተገልጧል። ጥናቱ፣ 18 በመቶ ያህሉ ኢትዮጵያዊያን ዓመቱን በከፋ የምግብ ዕጦት እንዳሳለፉና 42 በመቶዎቹ የሚኾኑት ደሞ አልፎ አልፎ ወይም ብዙ ጊዜ የምግብ እጥረት እንደገጠማቸው ማመልከቱንም ተቋሙ ጠቅሷል።