Get Mystery Box with random crypto!

የተሳሳተ መረጃ ስለማረም ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ በተለይም በቲክቶክ በተለቀቀ የተሳሳተ መረጃ የ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የተሳሳተ መረጃ ስለማረም

ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ በተለይም በቲክቶክ በተለቀቀ የተሳሳተ መረጃ የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝግባችሁ እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ ብቁ መሆን አለመሆናችሁን ባምቢስ በሚገኘው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ 5ኛ ፎቅ መታችሁ እንድታዩ በሚል የተለቀቀው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን  እየገለፅን ተመዝግባችሁ እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ ላተፈለገ እንግልት እንዳትዳረጉ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ይገልፃል፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እና ኮርፖሬሽኑ ነዋሪውን በተለይም ተመዝግቦ የሚጠባበቀውን የቤት ባለቤት ለማድረግ የተለያዩ የቤት ልማት አማራጮችን ተግባራዊ በማድረግ ከምንጊዜውም  በተሻለ መልኩ እየሰሩ እንደሚገኝ እየገለፅን ተመዝጋቢዎችም ሆነ ሌሎች ነዋሪዎች የተቋሙ ባልሆኑ ማህበራዊ ሚዲያዎችም ሆነ ግለሰቦች በሚያናፍሱት ወሬ እንዳትታለሉ እያስገነዘብን ትክክለኛውን የቤት መረጃ ለማግኘት ከታች ያሉትን የማህበራዊ ሚዲያ ሊንኮች ብቻ እንድትጠቀሙ እናሳስባለን፡፡ 

የአ/አ/ል/ አስተዳደር ቢሮ