Get Mystery Box with random crypto!

'ምሳ ከፍለን ብንበላም ውሃ በነፃ ነበር' ብለን ብንነግራቸው፣ ልጆቻችን እንዴት ያምኑናል?! | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

"ምሳ ከፍለን ብንበላም ውሃ በነፃ ነበር" ብለን ብንነግራቸው፣ ልጆቻችን እንዴት ያምኑናል?!

ድሮ ድሮ ምግብ ቤት ገብተን ሽሮ፣ በያይነቱ፣ ፓስታ በእንጀራ አሊያም ድንች በስጋ እናዝዝ ነበር። እና ውሃ በነፃ መሆኑ ግልጽ ነው። በጭራሽ ጥያቄም አይደለም። ምግብህን ከፍለህ ትበላና አንድ ጆግ ውሃ በነፃ ትጠጣለህ።

ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አስተናጋጆች አንድ ጥያቄ ይጠይቁ ጀመር፣ "የብርጭቆ ውሃ ወይንስ የታሸገ?!"። ምርጫህ የብርጭቆ ውሃ ከሆነ ምንም ንትርክ የለውም፤ ውሃ በጆግ ይመጣል። አንዳንድ ቦታ ጭራሽ በታጠነ ጆግ ነው የሚቀርብልህ።

በጊዜ ሂደት አስተናጋጆች ሌላ ጨዋታ ጀመሩ፤ "ይቅርታ የብርጭቆ ውሃ የለንም"። ንትርክ ተጀመረ ማለት ነው። ትንሽ ትነጫነጭና የታሸገ ውሃ ታዛለህ። ቢሆንም የውሃ ዋጋ አነስተኛ ነበር።

በመጨረሻ፣ የብርጭቆ ውሃ የሚባል ታሪክ ሆኖ አረፈ። አሁን ምግብ ቤት ገብተህ "የብርጭቆ ውሃ ይሁንልኝ" ማለት ነውር ነው፤ መሳቂያ መሆን ነው። ያለማጋነን የምግብ እና የውሃ ዋጋ መሳ ለመሳ ነው።

እና "ምሳ ከፍለን ብንበላም ውሃ በነፃ ነበር" ብለን ለልጆቻችን ብንነግራቸው ያምኑናል ወይ?!
Lami S