Get Mystery Box with random crypto!

በቀደም የአዲስ አበባ ከተማ አመራሮች ስለ ፒያሳና ሌሎች ፕሮጀክታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ሲ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

በቀደም የአዲስ አበባ ከተማ አመራሮች ስለ ፒያሳና ሌሎች ፕሮጀክታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ሲያቀርቡ እየሰማሁ ነበር፡፡ፒያሳ ስለነበሩባት ችግሮች ብዛት አብራርተው ሲጨርሱ አሁን የፒያሳ ነዋሪዎች በተላኩበት ቦታ ሽንት ቤት እንዳገኙ ፥ እንቅልፍ ተኝተው እያደሩም እንደሆነ ወዘተ ተነተኑ፡፡ብዙዎች ጥያቄ እንተወውና እንደው ግን የፒያሳ ልማት ለፒያሳ ህዝብ ጥቅም ከሆነ ጠቅላላ የፒያሳን ህዝብ በታትኖ ከማስወገድ እዚያው ፒያሳ ላይ ማስተካከል ይቻል ነበር፡፡ለምሳሌ ዶሮ ማነቂያን ብቻ ማንሳት ቢቻል እና እዚያ ቦታ የመኖሪያ ህንጻዎችን መገንባት ቢቻል የሚገነቡት የመኖሪያ ህንጻዎች የዶሮ ማነቂያን ህዝብ ብቻ ሳይሆን የጣልያን ሰፈርን እና የገዳም ሰፈርን ህዝብ መያዝ ይችሉ ነበር፡፡ከዚያም ገዳም ሰፈር እና ጣልያን ሰፈርን አልምቶ የእሪ በከንቱ እና ሌሎች ነዋሪዎችን ማኖር ይቻል ነበር፡፡ይሄ ብዙ ውስብስብ የሚባል እቅድ አልነበረም፡፡

የደጃች ውቤ ሰፈር ያኔ በኢህአዴግ ዘመን ከፈረሰ በኋላ ህይወታቸው የተመሳቀለ ፥ በድብርት ምክንያት የተጎዱ አረጋውያን ፥ ማህበራዊ መዋቅራቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች እስካሁን ድረስ አላገገሙም፡፡የአሁኑም ቢብስ እንጂ አያንስም፡፡

ማንኛውም ልማት የህዝብን ሁለገብ ጥቅም ታሳቢ ካላረገ ልማት ሊባል አይችልም፡፡

AB Bella