Get Mystery Box with random crypto!

መንግሥት በዋና ከተማ አዲስ አበባ የሚከናወኑ የቤት ፈረሳዎች ከተማዋን ለማዘመንና ለነዋሪዎቿም ምቹ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

መንግሥት በዋና ከተማ አዲስ አበባ የሚከናወኑ የቤት ፈረሳዎች ከተማዋን ለማዘመንና ለነዋሪዎቿም ምቹ ለማድረግ የታሰበ የልማት እቅድ መሆኑን ይገልጻል። መኖሪያ ቤታቸው ለፈረሰባቸው ወገኖችም ምትክ ቦታ እንደሚሰጥም እንዲሁ። በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ሥራ ሂደት መገምገሙንም ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በማኅበራዊ መገናኛ ገጻቸው አመልክተዋል። በዚህም ቀዳሚ ዓላማቸው አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ የተመቸች ሳቢ ከተማ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ማሳካት መሆኑንም ገልጸዋል። «የማልማት ሥራ ሂደቱ በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚና በመንግሥት ብሎም አነስተኛ ገቢ ባላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች እና የተለያዩ አካላት የተያዙና የተከራዩ ንብረቶችን የነካ ሊሆን ቢችልም ይህ ለረዥም ጊዜ ፋይዳ ትልም ይዞ የተነሳ ሥራ ሲጠናቀቅ ለሁሉም ባለድርሻ አካል ብሎም ለሰፊው ሕዝብ የሚሰጠው ጥቅም ትልቅ ነው»ም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ከተማን ለማዘመን በማሰብ የነባር ቤቶች እና መንደሮች መፍረስ አስቀድሞ ከሌሎች ሃገራት ተሞክሮ ቢወሰድበት መልካም እንደነበር የሚጠቁሙ በበኩላቸው ለታሪካዊ ሕንጻዎችና ቅርሶች ተገቢና ሞያዊ ጥንቃቄ እያሳሰቡ ነው። ከበቂ መተላለፊ መንገድ አንስቶ የመጸዳጃ ቤቶች እና የፍሳሽ ማውረጃ መስመሮች ጉድለት የሚታይባቸው ጭርንቁስ መንደሮችን የዋና ከተማዋን ደረጃ በጠበቀ መልኩ ማሻሻል እንደሚያስፈልግ የሚገልጹ ወገኖች ጥንታዊ የከተማ ገጽታዎችን ጠብቆ ማቆየት በሌሎች ሃገራት ለቱሪዝም መስህብነት አይነተኛ ሚና እንዳለውም ያነሳሉ።
DW