Get Mystery Box with random crypto!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ housinginaddisababa — Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች H
የቴሌግራም ቻናል አርማ housinginaddisababa — Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች
የሰርጥ አድራሻ: @housinginaddisababa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.64K
የሰርጥ መግለጫ

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates.

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-04-03 15:56:24
የአዲስ አበባ የመሬት አገልግሎት ስራ ጀምሯል
19.8K views12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 14:54:09
የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ጨረታ የአሸናፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አስገንብተው ለጨረታ ያቀረቧቸው የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር ከዚህ በታች  መመልከት ይቻላል።

ከዚህ በተጨማሪ በአዲስ ልሳን ጋዜጣ የመጋቢት 25/2016 እትም ማየት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን።
20.8K viewsedited  11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 22:58:37 #AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ #ለአፓርትመንት_ቤቶች እና #ለጋራ_መኖሪያ_ቤቶች ወይም ኮንዶሚኒየም ቤቶች አማካኝ የሽያጭ ዋጋ ተመን በ34 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ለሁሉም ክ/ከተሞች የአፈፃፀም መመሪያ መጻፉን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

በከተማዋ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተብሎ በገዥ እና ሻጭ መካከል የሚደረግ ውል ላይ የሚቀርበው ዋጋ እጅግ በተጋነነ መልኩ ዝቅተኛ በመሆኑ እና በባለሙያ የሚወሰድ የቤት ግምት ዋጋ ወቅታዊ ባመሆኑ መንግስት ከቤት ሽያጭ ተገቢውን ገቢ እየሰበሰበ እንዳልነበረ ቢሮው ገልጿል።

ይህንን ችግር ለመፍታት እንዲቻል ካለፈው ዓመት ሰኔ 8 ቀን 2015  ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ወቅታዊ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተግባራዊ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

ይሁን እንጂ በከተማ ደረጃ ተጠንቶ ተግባራዊ የተደረገ የቤት ሽያጭ ዋጋ እና አሰራሩ ላይ ከህብረተሰቡ በርካታ ቅሬታዎች እየቀረቡ በመሆኑ በመሬት ልማትና አስተዳደተር ቢሮ እና የመሬት ይዞታ ምዝገበና መረጃ አጄንሲ በጋራ ጥናት በማድረግ የተለዩ ክፍተቶችና እና የቤት ሽያጭ ግምት ላይ ማሻሻያ ተደርጓል ብሏል።

በተደረገው ማሻሻያ ለአፓርትመንት ቤቶች እና ኮንዶሚኒየም ቤቶች የሽያጭ ዋጋ ተመን አምና በሰኔ ወር ከነበረው 34 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።

በተሻሻለው  የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን መሰረት ከኮንደሚንየም እና አፓርትመንት ውጪ ለሆኑ ግንባታዎች፦

የግንባታ ነጠላ ዋጋ በጭቃ የተሰራ ቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 15,000 ብር፣
በብሎኬት የተሰራ የቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 20,000 ብር፣
የህንጻ ወለላቸው ከG+1 እስከ G+5 25,000 ብር እና፣
G+6 እና በላይ የሆኑ ቤት ወይም ህንጻ ነጠላ ዋጋ በካሬ 30,000 ተደርጓል፡፡

የቦታው መገኛ ዋጋ ('location value') ለከተማው የቦታ ደረጃ የጸደቀው ወቅታዊ አማካይ የሊዝ ጨረታ ዋጋ እንዲሆን መደረጉም ተገልጿል።

የቤት ስም ንብረት ዝውውር ክፍያ ማለትም አሹራ 4 በመቶ እና የቴምብር ቀረጥ 2 በመቶ ከጠቅላላ የቤቱ ሽያጭ ዋጋ ተሰልቶ ከ ከመጋቢት17 ቀን 2016 ዓ/ም  ጀምሮ እንዲከፈልም ቢሮ አዟል።

ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር  ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን #መሻሩንም ቢሮ ጠቅሷል።

በፍርድ ቤት እና በባንክ ሃራጅ ሽያጭ የስም ንብረት ዝውውር የሚጠየቅባቸው ይዞታዎችን በተመለከተ ይዞታ አገልግሎትና መብት ፈጠራ ደንብ ላይ በተቀመጠው አግባብ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል።

ይህ ማሻሻያ መምሪያ ከመውጣቱ በፊት የስም ንብረት ዝውውር አገልግሎት ጠይቀው በሂደት ላይ ሆኖ ክፍያ የፈጸሙ ተጋልጋዮች በቀድሞ አሰራር በከፈሉት ክፍያ መሰረት ይስተናገዳሉ ተብሏል።

ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ህንፃዎች የትመና ስራ የሚሰራላቸው ግንባታው በደረሰበት ወይም አሁን ላይ ባለበት ግንባታ ደረጃ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለሁሉም ክ/ከተሞች የፃፈውን የአፈፃፀም መመሪያ ዋቢ በማድረግ ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

Info - ShegerFm
Pic Credit - WZNews

@tikvahethiopia
20.7K views19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 22:58:35
16.5K views19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 22:25:55
በመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ላይ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ፤ በተቆጣጣሪ አካል እንዲወሰን የሚያደርግ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ

የተቆጣጣሪ አካሉ “የሀገሪቱን ነባራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች” ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ በየዓመቱ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ ዓመት የሚጸና የዋጋ ጭማሪ እንደሚያደርግ በአዲሱ አዋጅ ተደንግጓል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከጸደቀበት ዕለት ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆነው ይህ አዋጅ፤ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደርን ለመደንገግ የተዘጋጀ ነው። በስድስት ክፍሎች እና በሰላሳ ሁለት አንቀጾች የተዋቀረው አዋጁ፤ ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ እና ዋጋ፣ ውል የሚቋረጥባቸውን አካሄዶች፣ የተቆጣጣሪ አካል ስልጣን እና ተግባር እንዲሁም የጥቆማ እና ቅሬታ አቀራረብ ስነ ስርዓትን የተመለከቱ ድንጋጌዎችን በውስጡ አካትቷል።

“የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር” የሚመለከተው ይህ አዋጅ ከያዛቸው ድንጋጌዎች መካከል፤ “ነባር የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን” የተመለከተው ይገኝበታል። “አዋጁ ከመውጣቱ በፊት በጹሁፍ የተደረገ ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል፤ በአከራይ እና ተከራይ ስምምነት እንዲቋረጥ ካልተደረገ በስተቀር፤ በአግባቡ መረጋገጥ እና መመዝገብ እንዳለበት” በአዲሱ አዋጅ ላይ ሰፍሯል።

ውሉ መመዝገብ እና መረጋገጥ ያለበት፤ በዛሬው ዕለት በጸደቀው አዋጅ መሰረት የሚቋቋመው “ተቆጣጣሪ አካል”በተሰየመ በ30 ቀናት ውስጥ እንደሆነ በአዋጁ ተቀምጧል።ሆኖም የመኖሪያ ቤት ኪራይን ውል እና ዋጋን እንዲቆጣጠር በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች እና ክልሎች የሚመሰረተው አካል፤ የውል ማረጋገጫ እና የምዝገባ ጊዜውን እንዳስፈላጊነቱ እስከ ሶስት ወር ድረስ ሊያራዝም እንደሚችል በአዋጁ ተደንግጓል። https://ethiopiainsider.com/2024/12879/
17.5K views19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 22:22:05 አዲሱ አዋጅ “ስለ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል” ዘመን ምን ዝርዝር ይዟል?

ዛሬ በፓርላማ በጸደቀው “የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ” ከተዘረዘሩ ድንጋጌዎች ውስጥ፤ “የመኖሪያ ቤት የኪራይ ውል ዘመንን” የሚመለከቱት የሚጠቀሱ ናቸው። “የመኖሪያ ቤት ኪራይ የውል ዘመን ከሁለት ዓመት ሊያንስ አይችልም” ሲል የደነገገው አዋጁ፤ ይህ የተደረገበትን ዋነኛ ምክንያት በማብራሪያው ላይ አስፍሯል።

“የአዋጁ ዓላማ የመኖሪያ ቤት ኪራይ የተረጋጋ እንዲሆን ለማድረግ በመሆኑ፤ [ውሉ] ከሁለት ዓመት ያነሰ ቢሆን አከራዩ ውሉን ለማደስ ፍቃደኛ ላይሆን ስለሚችል፤ ተከራይ በየጊዜው በቀጣይ ስለሚከራየው ቤት በመጨነቅ የተረጋጋ ህይወት እንዳይመራ ያደርገዋል” ሲል የአዋጁ ማብራሪያ አትቷል። “ከሁለት ዓመት ያለፈ ዘመን ይኑረው ቢባል ደግሞ የአከራይን መብት እንዳይጫን፤ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ የውል ዘመኑ ከሁለት ዓመት ያላነሰ ጊዜ እንዲሆን” መደረጉን የአዋጁ ማብራሪያ አስገንዝቧል።

“አዋጁ ከመውጣቱ በፊት ከሁለት ዓመት በታች የተደረጉ የቤት ኪራይ ውሎች ላይ ይህንን አዋጅ ተግባራዊ ማድረግ ፍትሐዊ ስለማይሆን፤ በውላቸው ላይ ያጸደቁት ቤት ኪራይ የውል ዘመን ተቀባይነት እንዲያገኝ ተደርጓል” ሲል ማብራሪያው አክሏል። ከዚህ በተጨማሪ የውል ዘመን ሳይጠናቀቅ፤ የአንድ ቤት ባለቤትነት “በውርስ፣ በሽያጭ፣ በዕዳ ወይም በሌላ ማናቸውም ህጋዊ ምክንያት” ለሌላ ወገን ከተላለፈ፤ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውሉ ሊቋረጥ የሚችለው “ቤቱ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ የሚቆጠር የ6 ወር ማስጠንቀቂያ ለተከራይ በመስጠት ቤቱን እንዲለቅ ማድረግ እንደሚቻል ማብራሪያው” ደንግጓል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
15.3K views19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 22:14:05
አዲሱ አዋጅ “ስለ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል” ዘመን ምን ዝርዝር ይዟል?

• የቤት ኪራይ የውል ዘመን ከሁለት ዓመት ያነሰ ሊሆን አይችልም

• የቤት ኪራይ ውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ወይም “በመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ" ከተፈቀደው ውጭ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም

• 'የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ" ከመውጣቱ በፊት በጹሁፍ የተደረገ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ዘመን፤ በውሉ ላይ የተቀመጠው ዘመን ይሆናል

● የአንድ ቤት ባለቤትነት በውርስ፣ በሽያጭ፣ በዕዳ ወይም በሌላ ማናቸው ውም ህጋዊ ምክንያት ለሌላ ወገን ከተላለፈ፤ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውሉ ሊቋረጥ የሚችለው ቤቱ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ የ6 ወር ማስጠንቀቂያ ለተከራዩ በመስጠ ነጠት ነው

● ቤቱ ለሌላ ወገን የተላለፈው በስጦታ ከሆነ፤ ተከራይ የውል ዘመኑ እስኪያልቅ ድረስ በተከራየው ቤት የመቆየት መብት ይኖረዋል። የቤቱ ባለቤትነት በስጦታ የተላለፈለት ሰው፤ የቀድሞውን አከራይ ተክቶ በኪራይ ውሎ መሰረት የአከራይን መብቶች እና ግዴታዎች ይሸከማል

● ቤቱ የተላለፈለት አዲሱ የቤቱ ባለቤት ፈቃደኛ ከሆነ፤ ተከራይ ቤቱን እንደተከራየው ሊቀጥል ይችላል

● የኪራይ ውሉ የተቋረጠ የመኖሪያ ቤት ለሌላ ተከራይ የሚከራይ ከሆነ፤ “ “በመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ" መሰረት የሚደረግ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የቤቱ ኪራይ በተቋረጠው ውል ላይ የተቀመጠው የኪራይ ዋጋ ነው

ምንጭ፦ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ
16.4K viewsedited  19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 20:03:36
ከ 121 ሺ እስከ 95 ሺ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ስለማውጣት
******
በባንኩ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ያለአግባብ ከባንካችን የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ መሠረት 10 ሺ በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው መልሰዋል፡፡
የገንዘብ መጠኑ ከ 121 ሺ እስከ 95 ሺ ብር ያለአግባብ ከባንካችን ወስደው ያልመለሱ የግለሰቦችን ማንነት የሚያሳዩ መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ስላስፈለገ ለሁለተኛ ጊዜ ያወጣናቸውን መረጃዎች ከዚህ በታች ባለው ማስፈንጠሪያ መረጃዎችን መመልከት ይችላሉ ።
https://combanketh.et/customer-round-two
18.2K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 16:41:08
ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አስገንብተው ለጨረታ ያቀረቧቸው የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ጨረታ #አሸናፊዎች_ዝርዝር በነገው ዕለት ማለትም መጋቢት 25/2016 ዓ/ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ላይ በይፋ ይወጣል።
13.7K views13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 09:29:11
በፒያሳና አካባቢው እየተከናወነ ባለው የመንገድ ግንባታ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መንገዱ ስለተዘጋ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

ቀደም ሲል የመንገዱን መዘጋት በተመለከተ መረጃ ቢሰጥም አሁንም አሽከርካሪዎች ወደ ግንባታ ቦታው እየመጡ በግንባታ ስራው ላይ ጫና እየፈጠሩ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም በፒያሳና አካባቢው የመንገድ ግንባታ እየተከናወነ በመሆኑ ላልተወሰነ ጊዜ መንገዱ ስለተዘጋ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ በማለት አሳስቧል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

• ከጊዮርጊስ አደባባይ በእሳት አደጋ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከቅድስተ ማርያም ወደ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር

• ከአራት ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከባሻ ወልዴ ችሎት ወደ ቱሪስት እና ወደ ቅድስተ ማርያም

• ከእሪ በከንቱ (ቀይ ባህር ኮንዶሚኒየም) ወደ ደጎል አደባባይ እንዲሁም

• ከደጎል አደባባይ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ በሚወስዱት መንገዶች መግባት እና መንገዶቹን ለጊዜው መጠቀምም ሆነ በመንገዶቹ ላይ መኪና ማቆም እንደማይል ተገልጿል፡፡

ይህን በመመገንዘብ አሽከርካሪዎች ከእነዚህ ውጪ ያሉ ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ ፖሊስ አሳስቧል፡፡
16.3K views06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ