Get Mystery Box with random crypto!

በፒያሳና አካባቢው እየተከናወነ ባለው የመንገድ ግንባታ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መንገዱ ስለተዘጋ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

በፒያሳና አካባቢው እየተከናወነ ባለው የመንገድ ግንባታ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መንገዱ ስለተዘጋ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

ቀደም ሲል የመንገዱን መዘጋት በተመለከተ መረጃ ቢሰጥም አሁንም አሽከርካሪዎች ወደ ግንባታ ቦታው እየመጡ በግንባታ ስራው ላይ ጫና እየፈጠሩ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም በፒያሳና አካባቢው የመንገድ ግንባታ እየተከናወነ በመሆኑ ላልተወሰነ ጊዜ መንገዱ ስለተዘጋ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ በማለት አሳስቧል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

• ከጊዮርጊስ አደባባይ በእሳት አደጋ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከቅድስተ ማርያም ወደ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር

• ከአራት ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከባሻ ወልዴ ችሎት ወደ ቱሪስት እና ወደ ቅድስተ ማርያም

• ከእሪ በከንቱ (ቀይ ባህር ኮንዶሚኒየም) ወደ ደጎል አደባባይ እንዲሁም

• ከደጎል አደባባይ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ በሚወስዱት መንገዶች መግባት እና መንገዶቹን ለጊዜው መጠቀምም ሆነ በመንገዶቹ ላይ መኪና ማቆም እንደማይል ተገልጿል፡፡

ይህን በመመገንዘብ አሽከርካሪዎች ከእነዚህ ውጪ ያሉ ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ ፖሊስ አሳስቧል፡፡