Get Mystery Box with random crypto!

አዲሱ አዋጅ “ስለ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል” ዘመን ምን ዝርዝር ይዟል? • የቤት ኪራይ የውል ዘመ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

አዲሱ አዋጅ “ስለ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል” ዘመን ምን ዝርዝር ይዟል?

• የቤት ኪራይ የውል ዘመን ከሁለት ዓመት ያነሰ ሊሆን አይችልም

• የቤት ኪራይ ውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ወይም “በመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ" ከተፈቀደው ውጭ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም

• 'የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ" ከመውጣቱ በፊት በጹሁፍ የተደረገ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ዘመን፤ በውሉ ላይ የተቀመጠው ዘመን ይሆናል

● የአንድ ቤት ባለቤትነት በውርስ፣ በሽያጭ፣ በዕዳ ወይም በሌላ ማናቸው ውም ህጋዊ ምክንያት ለሌላ ወገን ከተላለፈ፤ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውሉ ሊቋረጥ የሚችለው ቤቱ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ የ6 ወር ማስጠንቀቂያ ለተከራዩ በመስጠ ነጠት ነው

● ቤቱ ለሌላ ወገን የተላለፈው በስጦታ ከሆነ፤ ተከራይ የውል ዘመኑ እስኪያልቅ ድረስ በተከራየው ቤት የመቆየት መብት ይኖረዋል። የቤቱ ባለቤትነት በስጦታ የተላለፈለት ሰው፤ የቀድሞውን አከራይ ተክቶ በኪራይ ውሎ መሰረት የአከራይን መብቶች እና ግዴታዎች ይሸከማል

● ቤቱ የተላለፈለት አዲሱ የቤቱ ባለቤት ፈቃደኛ ከሆነ፤ ተከራይ ቤቱን እንደተከራየው ሊቀጥል ይችላል

● የኪራይ ውሉ የተቋረጠ የመኖሪያ ቤት ለሌላ ተከራይ የሚከራይ ከሆነ፤ “ “በመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ" መሰረት የሚደረግ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የቤቱ ኪራይ በተቋረጠው ውል ላይ የተቀመጠው የኪራይ ዋጋ ነው

ምንጭ፦ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ