Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የሰርጥ አድራሻ: @gitmnamuzika
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.30K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብበት ቻናል ነው ይከታተሉ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ ሚክስ ከፌሊኖቫ ጋር
Creator@fellynovaa
Invite link to share
https://t.me/ vKDN0lXKiKFmN2M0

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-03-30 15:24:12 አራተኛ ቀን

እስከዛሬ ምንም ነገር አልተፈጠረም፤ ዛሬ ግን መፈጠር አለበት ስል አሰብኩ።

ቀኑ አልመሽልህ ብሎኝ ስቁነጠነጥ ፤ መኝታዬ ሆኜ ጠበኳት፤ ዘግይታ( ወይንስ የዘገየች ስለመሰለኝ ነው??) መብራቱን አጠፋች። ትመጣለች ብዬ ብጠብቅ ሳትመጣ ቀረች።

ብቻዬን ከሀሳቤ ጋር ትታኝ ወደ ምኝታዋ ሄደች።

ነገሮች ዕንቆቅልሽ ናቸው፤ ሳልፈቅድላት መጥታ መኝታዬን ተጋራች፤ ሳልጠራት መጥታ በምኞት ወጠረችኝ፤ ደሞኮ ጧት ማታ ምንም እንዳልተፈጠረ ነው የምትሆነው፤ ሴት ልጅ ሁና ማታ እንዳልተቃቀፉ እንዳልተባበሱ፤ እንዴት ጧት ስታዬው አታፍረውም??

አንዳንዴ ማታ አብረን ያሳለፍን አይመስለኝም ። እየቃዠሁ ይሆን?? ሁሉም ነገር በምናቡ የተፈጠረ ቢሆንስ? ወይንስ ችግሩ ከሷ ነው?? የማስታወስ ችግር ይኖርባት ይሆን?? ወይንስ እያስመሰለች?? እያስመሰለች ከነበረ፤ በጣም የተለየ ተሰጥዖ አላት ማለት ነው።
447 views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 15:23:46 ሦስተኛ ቀን

መጥታ አጠገቤ ስትጋደም፤ ዕንቅልፍ አልወሰደኝም ነበር። ልቤ ትር ትር ስትል ይሰማኝ ነበር። ከላይ ተራቁታ ፤ ከታች በውስጥ ልብስ ብቻ ነበረች። መብራቱ ስለጠፋ ባላየውም አረንጓዴ ወይንም ሰማያዊ ውስጥ ልብስ ይመስለኛል። ለምን እንዲ እንደሚሰማኝ አላውቅም ጨዋ ልጅ ነበርኩ፤ ኩሩ፤ እንኳን ከሰራተኛ ጋር ልከሰከስ ይቅርና በተለያየ አጋጣሚ ስለ ውበቴ ያሞገሱኝን የከተማ ቆነጃጅትን በሩቁ ነበር የምሸሸው። እንኳን የሴት የወንድ ጓደኞቼ ራሱ ጥቂት ናቸው ከነሱ ጋር እንኳን ብዙም አልግባባቸውም።

አስቀያሚዋ ሰራተኛችን ግን ፤ ምሽት አጠገቤ ስትተኛ የቀኗን አስቀያሚነት ዘንግታ የምሽት ልዕልት ትሆናለች። የሆነ በተረቱ ዓለም ዕንደምናውቃቸው መተት ተደርጎባቸው ወደ አስቀያሚነት እንደሚለወጡ ልዕልቶች፤ መተቱ ወይንም ዕርግማኑ የሚሰበረው ዕውነተኛ ፍቅር ስታገኝ ነው ።

የኔ ግን ዕውነተኛ ፍቅር አይመስለኝም፤ ምሽት ላይ ዕንጂ ቀን ላይ ከነመፈጠሯ እረሳታለሁ። ያቺ ጎዛዛ ሰራተኛ ናት ሌሊት ሲሆን ዕንደዛ በቅልጥፍና ያቀፈችኝ?? ያቺ ገጠሬ ሰራተኛ ናት ምሽት ላይ ሰውነቷን እንደ ለስላሳ ሙዚቃ የምታንቀሳቅሰው?? ምሽት ላይኮ ፤ በቃ ያ ቀርፋፋ ደባሪ እሷነቷ የለም።
416 views12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 15:23:17 ሦስተኛ ቀን

እንደምንም መደፈር እንዳለበት ወሰነ፤ በበነጋታው በአምስተኛው ቀን ቤተሰቦቹ ይመለሳሉ።

የቀረው የብቸኝነት ግዜ ዛሬና ነገ ነው። ወይ ዛሬ ወይ ነገ አብሯት ማደር እንዳለበት ወስኗል።

ምሽት ሆነ

አጠገቡ መጥታ ተኛች፤ የተወሰኑ ደቂቃዎችን በትዕግስት ከጠበቀ በሗላ እንደምንም ዕጆቹን ትከሻዋ ላይ አሳረፈ። ቀስ እያለ ወደ ታች፤
403 views12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 14:54:16 ይህ ከሆነ ፤ በቀጣዩ ቀን ጧት ከዕንቅልፉ ሲነቃ ፤ አጠገቡ ተኝታ የነበረችውን ሰራተኛ አጣት፤ ቀደም ብላ ከዕንቅልፏ ተነስታ ኖሯል።

ሌሊቱን ሙሉ የሚፈጠረውን በትዕግስት ሲጠባበቅ ቆይቶ ነበር ሊነጋ ሲል ዕንቅልፍ የወሰደው።

ከመኝታው ተነስቶ ወደ ሳሎን ሲገባ፤ ሰራተኛዋ ቤቱን እየጠረገች አገኛት።ምንም አዲስ ነገር እንዳልተፈጠረ ሁኔታዋ፤ ሶፋው ላይ ተቀምጦ ፊቷን አትኩሮ ተመለከ፤ ታፍር እንደሁ በሚል ግን ምንም ነገር ፊቷ ላይ አልሳለችም፤ ሳሎን መቀመጡንም ያስተዋለች አልመሰለችም።


መሸ።

ሁለተኛ ቀን

አሁንም መብራቱ ከጠፋ በሗላ ሰራተኛዋ መጥታ አጠገቡ ተጋደመች። አላስቻለውም ዕጆቹን በአንገቷ ዙርያ አድርጎ ሊያቅፋትና ሁለመናዋን ሊዳብሳት ከጀለ።

ጀርባዋን ሰጥታው ነበር የተኛችው፤ ቀስ ብሎ ተጠጋት ፤ ሰውነታቸው ተነካኩ።

ዕጆቹን ሲያልበው ይሰማዋል፤ ቀስ አድርጎ ዕጆቹን ክንዶቿ ለማድረግ ቃጣ ግን አልቻለም፤ ዕጆቹ ተንቀጠቀጡ።





ይቀጥላል


ቀጣዩ ክፍል እንዲደርሳቹ ቻናሉን subscribe ማድረግ እንዳትረሱ
496 views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 09:50:30 ልቡ ክው አለች፤ በቤቱ ውስጥ ከሱና ከሰራተኛቸው በስተቀር ምንም እንደሌለ አሰበና ተረጋጋ። አጠገቡ የተኛችው ሴት ስለመሆኗ በረጅም ፀጉሯ ተረድቷል።

ለመጀመሪያ ግዜ ስለ ሰራተኛቸው መልክ ማሰብ ጀመረ፤ ረጅም ጥቁር ፀጉር፤ ትንንሽ ዓይኖች፤ ድርቅ ያለ ከንፈር፤ቆራጣ አፍንጫ፤ ነጭ የቆዳ ቀለም፤ ምንም የሚስብ ነገር የሌለው ጣረሞት ፊት።


አጠገቡ የተኛችውን ሴት ፊት መለየት አልቻለም፤ ጀርባዋን ሰጥታው ነበር የተኛችው።

ሰራተኛዋ ከሆነች ስለምን የራሷን መኝታ ትታ እርሱ ጋ መጣች??

አዕምሮው ሌላ ነገር ማሰብ ጀመረ፤ ግን ከመጣችስ በሗላ ጀርባ ሰጥቶ መተኛትን ምን ይሉታል??

ግራ ተጋባ፤ ሁኔታዎችን በትዕግስት ሊጠብቅና ከሷ ምንም ዓይነት ምላሽ እስካላገኘ ድረስ ላይነካት ቃል ገባ።

























100 views06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 06:50:13 ክረምቱ ሲመጣ ብዙ ነገሮች አብረው ይመጣሉ፤ ትምህርት ይዘጋል፤ ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ይሄዳሉ፤ የተነፋፍቁ የዝናብ ጠብታዎችና የመሬት አቧራዎች ሲተቃቀፉ ዓየሩን በጠረናቸው ያውዱታል።

የተጠበሰ የበቆሎ እሸት ሻጮች ክሰላቸውን እየሞቁ ከ ብርዱ ጋር ፉክክር ይገጥማሉ።

ክረምቱ ሲመጣ የዮሮና አባት ለክረምት ትምህርት ይሄዳል፤ እናቱና እህቱም ገጠር አያታቸውን ሊጠይቁ ይሄዳሉ።

ቤት ውስጥ ዮሮና ና መልከጥፉ ሠራተኛቸው ብቻ ቀርተዋል።


አንድ ቀን ምሽት ፤ መብራቱ እንደጠፋ የሆነ ሰው መጥቶ አጠገቡ ተጋደመ። ልቡ ክው አለች፤ በጣም ደነገጠ።






ይቀጥላል



@yaviye
412 views03:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 06:48:40 ዮሮና

"ኧረ ዮሮና" ተጣራች እናቱ

ዮ ሮና

ዮ _ ሮ_ና

ቃላቶቹን አንድ በአንድ እየረገጠች ተጣራች።

ደጅ ከልጆች ጋር እየተጫወተ ነበር።

ስሙን ስትጠራው አጠራሯ ያበሽቀዋል።

ቶሎ ካልመለሰላት አከታትላ ትጣራለች።

























392 views03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 06:45:39 በለመለመው ሜዳ ተማሪዎች እየተሯሯጡ ሲጫወቱ ይታየዋል፤ ሳሮቹ አልተከረከሙም ፤ የሳሩ ጤዛ አልደረቀም፤ ሂሪያ የሚጫወቱ ሕፃናት በቡድን ተከፋፍለው ይፋለማሉ፤ አባሮሽ የሚጫወቱትም ይሯሯጣሉ ።

" ዮሮና" አለች መምህሯ በተቆጣ ድምፅ።
ዮሮና ከመስኮቱ ትዕይንት ዓይኖቹን መለሰ። ክፍል ውስጥ እንደነበር ዘንግቶት ኖሯል።

"ዑስፑና ናዓው ጊሽን ዐፑኔ??" መምህሯ ጠየቀች።









ይቀጥላል
377 views03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 09:54:34 የዜግነት ክብር
ተምሬ ያደግሁት...
የዜግነት ክብር በማለት ዘምሬ
class የምገባ...
ስለ ሰንደቅ ክብር ብዙ ተመክሬ
ከክላስ ውስጥ ደግሞ...
የቀለሙን ትርጉም በ civics ተምሬ
እንዲህ ነው ያደግሁት...
ሶስቱንም ቀለም...
በወርድ እና እርዝመት በእኩል ቀምሬ
እንዲህ ነው ያደግሁት...
.ልዩነታችንን እንደ ጌጥ ቆጥሬ
እንዲህ ነው ያደግሁት...
የክልልን ትርጉም
ብዙውን ሳላውቀው ብዙ ሳልረዳ
አስራ አንዱን ክልል
ሁሉንም አይቼ እንደ እናቴ ጓዳ
ሁሉን ቋንቋ ልወርስ
ሀሳቤን ስሸክፍ ምኞቴን ስነዳ
እንዲህ ነው ያደግሁት...
በሶስቱ ቀለም በአንድ ሰንደቅ ታጥሬ አረንጓዴ...ቢጫ...ቀይ
በልቤ ዙፋን ላይ በእኩል ቀምሬ
ታድያ ምነው ዛሬ
አረንጓዴ ቢጫው ቀለሙ እየጠፋ
ቀዩ ቀለም ብቻ ከሰንደቁ ሠፋ
የዜግነት ክብር...
@peom_by_peom
by Belaya
663 views06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 23:00:51
ሁሌም አንድ ነገር አዕምሮዬን ይወዘውዘዋል !
እሱም ሀገሬ ለእኛ ምንም አታድርግ  በዛ አልቀዬማትም.. ግን እኔ ላደርግላት ምፈልገውን ሳላደርግ እንደምቀር ሲሰማኚ በእውነቱ አዝናለው!!...
አንድ መራራ እውነት አለ "ሀገር የላችሁም" እናንተ ምትፈልጉላትን ነገር አልማቹሁላት ግን እንዳታኖሯት እዬኖረች ስታዬት ምን ይሰማቹኋል ?...

ሰው ያለህልሙ እያለመ ቅዥቱ እና እውነቱ እንደ ደመና መንገድ ከኋላ እዬጠፍ ነው !!..
ለሀገራችሁ ልታደርጉ የምታልሙትን ሳታደርጉ እንደመቅረት ምን ህመም አለ...?

ምንም ቢሆን ደሞ ሀገርን ማጣት አንፈልግም አይድል ??

እሷ ልታደርግ ሚገባውንም ባታደርግ እኛ ልናደርግ ያለምንላትን ሳናኖራት ብንቀርም እንኳ እቺን ሀገር ከአንጀት የቀጠነች ግን ለሰውነት መቆሚያችን ምሰሶስ አይደለች ??!

ኢትዬጵያ ? ግን ? ለሰው መሆናችን ታስፈልጊናለሽ !!

____
@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
296 views20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ