Get Mystery Box with random crypto!

አራተኛ ቀን እስከዛሬ ምንም ነገር አልተፈጠረም፤ ዛሬ ግን መፈጠር አለበት ስል አሰብኩ። ቀኑ አ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

አራተኛ ቀን

እስከዛሬ ምንም ነገር አልተፈጠረም፤ ዛሬ ግን መፈጠር አለበት ስል አሰብኩ።

ቀኑ አልመሽልህ ብሎኝ ስቁነጠነጥ ፤ መኝታዬ ሆኜ ጠበኳት፤ ዘግይታ( ወይንስ የዘገየች ስለመሰለኝ ነው??) መብራቱን አጠፋች። ትመጣለች ብዬ ብጠብቅ ሳትመጣ ቀረች።

ብቻዬን ከሀሳቤ ጋር ትታኝ ወደ ምኝታዋ ሄደች።

ነገሮች ዕንቆቅልሽ ናቸው፤ ሳልፈቅድላት መጥታ መኝታዬን ተጋራች፤ ሳልጠራት መጥታ በምኞት ወጠረችኝ፤ ደሞኮ ጧት ማታ ምንም እንዳልተፈጠረ ነው የምትሆነው፤ ሴት ልጅ ሁና ማታ እንዳልተቃቀፉ እንዳልተባበሱ፤ እንዴት ጧት ስታዬው አታፍረውም??

አንዳንዴ ማታ አብረን ያሳለፍን አይመስለኝም ። እየቃዠሁ ይሆን?? ሁሉም ነገር በምናቡ የተፈጠረ ቢሆንስ? ወይንስ ችግሩ ከሷ ነው?? የማስታወስ ችግር ይኖርባት ይሆን?? ወይንስ እያስመሰለች?? እያስመሰለች ከነበረ፤ በጣም የተለየ ተሰጥዖ አላት ማለት ነው።