Get Mystery Box with random crypto!

ሦስተኛ ቀን መጥታ አጠገቤ ስትጋደም፤ ዕንቅልፍ አልወሰደኝም ነበር። ልቤ ትር ትር ስትል ይሰማኝ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ሦስተኛ ቀን

መጥታ አጠገቤ ስትጋደም፤ ዕንቅልፍ አልወሰደኝም ነበር። ልቤ ትር ትር ስትል ይሰማኝ ነበር። ከላይ ተራቁታ ፤ ከታች በውስጥ ልብስ ብቻ ነበረች። መብራቱ ስለጠፋ ባላየውም አረንጓዴ ወይንም ሰማያዊ ውስጥ ልብስ ይመስለኛል። ለምን እንዲ እንደሚሰማኝ አላውቅም ጨዋ ልጅ ነበርኩ፤ ኩሩ፤ እንኳን ከሰራተኛ ጋር ልከሰከስ ይቅርና በተለያየ አጋጣሚ ስለ ውበቴ ያሞገሱኝን የከተማ ቆነጃጅትን በሩቁ ነበር የምሸሸው። እንኳን የሴት የወንድ ጓደኞቼ ራሱ ጥቂት ናቸው ከነሱ ጋር እንኳን ብዙም አልግባባቸውም።

አስቀያሚዋ ሰራተኛችን ግን ፤ ምሽት አጠገቤ ስትተኛ የቀኗን አስቀያሚነት ዘንግታ የምሽት ልዕልት ትሆናለች። የሆነ በተረቱ ዓለም ዕንደምናውቃቸው መተት ተደርጎባቸው ወደ አስቀያሚነት እንደሚለወጡ ልዕልቶች፤ መተቱ ወይንም ዕርግማኑ የሚሰበረው ዕውነተኛ ፍቅር ስታገኝ ነው ።

የኔ ግን ዕውነተኛ ፍቅር አይመስለኝም፤ ምሽት ላይ ዕንጂ ቀን ላይ ከነመፈጠሯ እረሳታለሁ። ያቺ ጎዛዛ ሰራተኛ ናት ሌሊት ሲሆን ዕንደዛ በቅልጥፍና ያቀፈችኝ?? ያቺ ገጠሬ ሰራተኛ ናት ምሽት ላይ ሰውነቷን እንደ ለስላሳ ሙዚቃ የምታንቀሳቅሰው?? ምሽት ላይኮ ፤ በቃ ያ ቀርፋፋ ደባሪ እሷነቷ የለም።