Get Mystery Box with random crypto!

የነ ዮሮና ሰራተኛ ታማ ፀበል ገባች። በሰፈሩ ስለሷ ብዙ ተወራ፤ ሌሊት በዕንቅልፍ ልቧ የመጓዝ ልማ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የነ ዮሮና ሰራተኛ ታማ ፀበል ገባች። በሰፈሩ ስለሷ ብዙ ተወራ፤ ሌሊት በዕንቅልፍ ልቧ የመጓዝ ልማድ ነበረባት አሉ። አንዳንዶች ደግሞ በዘር የሚዋረስ ዛር አለባት አሉ። ሌሎችም በቀትር ወንዝ ስትሄድ ጋኔል ለክፏት ነው አሉ።


ዕንጨት ሰበራ ስትሄድ ፤ ጫካ ውስጥ ቡና የሚጠጡ ሰይጣኖችን ደርሳባቸው ነው በሽተኛ ያረጓት።

ብዙ ብዙ ተባለ፤ ቡዳ በልቷት ነው ያሉም አሉ።

ዮሮና ግን ምሽት አብረው ያሳለፉት፤ ትዝታው ብቻ በአዕምሮው ቀረ። ደጋግሞ ስለነዛ ምሽቶች ያልማል።