Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የሰርጥ አድራሻ: @gitmnamuzika
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.30K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብበት ቻናል ነው ይከታተሉ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ ሚክስ ከፌሊኖቫ ጋር
Creator@fellynovaa
Invite link to share
https://t.me/ vKDN0lXKiKFmN2M0

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-05-03 00:07:56 #ለፈገግታ
#የቲጂዋ_ፍቅሬ
#ግፍ_አይሆንብሽም
ገንዘቤን ገፍግፌ፣
ኪሴን አራግፌ።
ጊዜዬን ገድዬ፣
ሰዓትን በድዬ።
ባይኔ አፍጥጬ፣
ብሌኔን ቆንጥጬ።
ስጠብቅሽ ስውል፣
አፍርሼ ውል።
ስትዘልቂ በፈገግታ፣
ልቤ ሀሴት አግታ።
በዝምታ ስትቀጪኝ፣
በስንብት ስትንጪኝ።
ትተሽኝ ስታመሪ፣
ሀዘኔን ስታበጂለት መሪ።
ሌላ ምንም አልልሽም፣
ብቻ ግፍ አይሆንብሽም!?
16/12/2008
#መኮንን_ዮሴፍ
Fb ላይ ተፃፈ
799 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 21:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 00:07:56 #አሟሟት
አወዳደቅ አይነት አለው ፈርጅ፣
የብርዝ አወቃቀር እንደሆነው ጠጅ።
ያኔ ገና አንቺ ላይ ሲጥለኝ፣
አሰባበሬን ፈራሁት እንዳይገነጥለኝ።
ማልቀስ አምሮኝ ነበር ከዛፍ እንደተፈጠፈጠ፣
ግን ዋጥኩት አይቻልም ብዬ ካልተጋፈጠ።
የሰው አጥር አናት ቆመው፣
ከግንብ ከተንሸራተቱ ቀድመው።
መች ያሽና የዘንድሮ ወጌሻ፣
ዘዴ አለኝ ብሎ ለቅምሻ።
ቢቋምጥ ገረመኝ ለምላሴ እጥፋት፣
ወደሱ መምጣቴ እኮ ነው የኔ ጥፋት።
እንደው ስራመድ ስሬ ዞሮ፣
ጓዴ ቢያመጣኝ እንዲመልሱት አብሮ።
እንኳን ሊያሽለኝ አለብኝ ባስ፣
እንዴት ልድረስ አንቺ ጋርስ።
አካሄዴም መርገጥ እዚና እዛ፣
በቆሎ ብላ አትበይኝ የጠነዛ።
አይደለም እሸት ወዳጄ እሸቱም አልበጀ፣
የዚ ዘመን በሽታ ካላንገላጀጀ፣
ይተው መስሎሻል አፍልቶ ዝንጅብል፣
በሻይ አይፈታም የፋሻ ጥቅልል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ማቀፍና መጭመቅ የተምታታብሽ ፍጡር፣
አድኜ ብሸክፍልሽ የሚጋጥ ከዱር።
ከነፈረው አንጀቴ ዘለሽ ብትጠመጠሚ፣
ቁጢጥ እንዳልኩ ቀረሁልሽ አይ አጋጣሚ።
ያሳርራልና የኩሽናሽ መጥበሻ፣
መክደኛ ስሪለት አፉን ማልበሻ።
እንጨቱ ቤትሽ ጭቃ ተመረገ፣
ምናለ ትያለሽ ለውርጭ ካልዳረገ።
ባይጠፋም ከመደብሽ ቁርበት ለመተኛ፣
በጎችሽ አለቁ በአጎዛሽ መሸኛ።
ሴት አደረገሽ እንጂ አቤት ስትበልቺ፣
ቆዳ በሳው ብለሽ መቆራረጥ አትሰልቺ።
አትከፊ ከበሮ ይወጠራል ተልጎ፣
ማን ይደክማል ጀሪካን ፈልጎ።
የሠረጋችን ለታ ደብዳቢው እጁ ጉዱ ፈላ፣
እስክስታ ለሚያስወርድ ዘፈን ካላደላ።
እጮኛ አያገኝም ካልማረካት ምቱ፣
ይሻለዋል በቃ በሽምደዳ መሰንበቱ።
ከጭፈራው ቦታ ካልገባ አጥንቶ፣
ፍቅሩን አይወስድም ከልቧ አፅንቶ።
በእንጋጠም ምክንያት ይዞ ካላሽኮረመመ፣
ለጥየቃ ጉብኝት የውሸት ካልታመመ።
ከሰማይ አትወርድም ከምድር አትበቅልም፣
ካልቀለበ ቶሎ የአይኖቿን ስልምልም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከድግሱ መልስ ቀርቻለሁ ከአልጋ፣
ወረተኛው መውደዷ ከኔ ባይጠጋ።
አሁንስ ልፀልይ አሟሟቴን አሳምረው፣
በፍቅሯ ህመም ውስጤን አትወግረው።
ጥሎሽ ካልተሰጠ ሚስት ትነጠቃለች፣
ሰማንያዋ ፈርሶ የራስነት ታበቃለች።
ያስተናገደሽ ጎጀዬ አስለትሞ ቆርቆሮ፣
በእርግቦች መናቆር ሆንኩልሽ ደንቆሮ።
ምነው አምላኬ ከምትገለኝ በኦና፣
እሷን ባታስለምደኝ ያኔ ገና።
መዘባበቻ መጠቋቆሚያ መደምደሚያ ፍፃሜዬ፣
ማፍቀሬ ነበር ወይ ብልሹ ስራዬ።
እስኪብርቶው ሳይከደን ፊርማችን ሳይደርቅ፣
የትዳራችን መንኮታኮት ከድጋፉ ማለቅ።
ምን ሚሉት ጨዋታ ምን ሚሉት ቅዠት፣
በፈሰሰ ኃይል መዶል ውሸት።
አሁንስ ልፀልይ ጣሬን አታብዛው፣
በማፍቀር ስቃይ ሀዘኔን አትግዛው።
ምትፈታተን ህይወት እስከመጨረሻ ህቅታ፣
ኩርኩም የምትጨምር ከእንቅልፍ አንቅታ።
የለም ቃሏ ከፍራሽህ ስትባንን፣
የምታበረታታ እርኩስ ግለኝነትን።
አትፍረጂብኝ ፍቅርሽ ነው ሚያፈላስመኝ፣
በመጫር ውስጥ ከጭነት ሚከተኝ።
በብዕር ዝምታ እንደእብድ አስለፍልፎ፣
ድምፄን የሚያራግፍ ከጥሞናዬ አልፎ።
አወዳደቄ ያላመረ አሟሟቴ አይሰምርም፣
ካልመጣሽ አሰባበሬ መወላለቅ መሆኑ አይቀርም።
#መኮንን_ዮሴፍ
840 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 21:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 16:05:35 ግን እወድሻለሁ
----------------------
እንዳይከፋሽ ውዴ...

ናፍቄሀለሁ ወይ? ብለሽ ያልሽኝ ለታ
ራሴ ናፍቆኛል
ብየ ነው የምልሽ ያላንዳች ይሉኝታ

ትወደኛለህ ወይ? ብለሽ ያልሽኝ ጊዜ
እኔን እወዳለሁ
ብየ ነው የምልሽ ያላንዳች ትካዜ

ታምነኛለህ እንዴ? ብለሽ ከጠየቅሽኝ
እራሴን አምናለሁ
ብየ ነው የምልሽ ምንም ቅር ሳይለኝ

እንዳይከፋሽ ውዴ...
ላንች ስትጠይቂኝ ለእኔ የምመልስ
ቀውሼ አደለም ወይም አጥቼ መልስ
ምክንያቱ ይሄ ነው

አጥንቴ ካጥንትሽ
ደምሽ ከደሜ ጋር ስለተዋሀደ
ይህ ሚስኪን መንፈሴ
አንችን አይጠላሽም እኔን ከወደደ!!!

By belaya

https://t.me/poem_by_poem
2.1K viewsbelaya, 13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 01:12:46 ሲባል እሰማለሁ
"ህይወትን አሸንፍ"
መኖር አይበልጥም ወይ
ከመወዳደር ጽንፍ?

እንደሆን ነው እንጂ
የልቡን መቃብር በሳቅ የከለለ
ህይወት ስትሸነፍ ያየ ሰው የት አለ?

ምንደነው መሸነፍ?
ማንን ነው ማሸነፍ ?

ለይመሰል ነው እንጂ እንዲያው ተዘክሮ
መች ይወዳደራል ነዋሪና ኑሮ?

ወዴት ነው መድረሻ የት ነው መነሻዬ?
:
መኖር አይደለም ወይ የመኖር ድርሻዬ?

ሀገሬው መረሬው
"ቀንህን ብለጠው" ብሎ ይለፍፋል
እውነት በሰው አቅም ህይወት ይሸነፋል?

ኤልያስ ሽታኹን https://t.me/poem_by_poem
2.2K viewsbelaya, 22:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 21:04:37 ባላነበው እኔ ያትሮኖሱን ያሃል፣

መቅረት ነው ትርጉሙ ከመገኜት መሃል፣

መምጣትሽን አይነግርም ፊደሉም ተረግሟል፣

___
ገጣሚ ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat
@geez_mulat

ለምትወዱት በሙሉ ሼር አድርጉላቸው
2.0K viewsጥ ቁር ዝምታ, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 16:24:04 ወይዘሮ ቅናት


ስለምትቀና የራሷን ኑሮ ከሌሎች ጋር ዕያነፃፀረች ታማርራለች፤ ደስተኛ ሰው ስታይ ስለምትቀና ትተናኮስና የሰውን ደስታ በማጨለም ትረካለች። በዚህም ምክንያት ደስታዋም በሌሎች ሰዎች ሐዘን ላይ የተመሰረተ ይሆናል።

ከዮሮና እህት ማስቀናት ጋር የሚጣሉት ብዙን ጊዜ በዚህ ባህሪዋ ነው ።
2.3K viewsያቢ ነኝ, 13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 16:23:47 እስቲ አሁን ደግሞ የዮሮናን ቤተሰቦች እናስተዋውቃችሁ።

እናቱ ቅናት ትባላለች። የብርድ በሽታ አለባት ፤ ቁርጥማት ያሰቃያታል በተለይ የግራ እጇና እግሯ ለ ብርድ በሽታ የተጋለጠ ነው ።



እህቱ ደግሞ ማስቀናት ትባላለች።


አባቱ ደግሞ አባ ኩራት ይባላሉ፤ እዚህ ዓለም ላይ ከክብራቸው የሚበልጥባቸው ነገር የለም።

ማስቀናት ሰዎች እንዲቀኑባት ትፈልጋለች ፤ ብትቸገር ዕንኳን ተቸግሬያለሁ አትልም።

ምሬትን አታውቅም፤ ሁልጊዜ ስል ጥሩ ጎኗ ዕና ስለተመቻቸ ኑሮዋ ነው የምታወራው።


ፌስቡክ ላይ አሪፍ አሪፍ እየለበሰች፤ ዓሪፍ ዓሪፍ ዕየተመገበች መፖሰት ያስደስታታል።


መዝናኛ ቦታዎች ሄዳ ፎቶ ካልተነሳች፤ የተዝናናች አይመስላት።( የተነሳቻቸውን ፎቶዎች ለ ጓደኞቿ በማሳየት ለማስቀናት)

በዚህም ምክንያት ጓደኞቿ ስለሚቀኑባት አይወዷትም።





































2.2K viewsያቢ ነኝ, 13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 15:06:25 አዎ እኔ ደህና ነኝ

አዎ እኔ ደህና ነኝ፣
ብቻ ዝም ብሎ እራሴን ያመኛል
የወገኔ ስቃይ፣
አንቅልፍ እየነሳ ይቀሰቅሰኛል!
አዎ እኔ ደህና ነኝ፣
ሽብር አናውዞታል የልቤን ከተማ
ሰው በሞተ ቁጠር፣
ደረት እየደቃሁ አበራለሁ ሻማ!
አዎ እኔ ደህናነኝ፣
እብደት ተጠግቶኝ ዝም ብዬ ስቃለሁ
ሀገሬ ቁጭ ብዬ፣
ልክ እንደ ባይተዋር ሀገር ናፍቃለሁ!
አዎ እኔ ደህና ነኝ፣
ወገኔ ባልኩት ሰው ዘመኔን ምጉላላ
ሆዴን እየራበው፣
በቀን ሀያ ግዜ መከራ ምበላ!
እናም፣
ሀዘን አሰቃይቶኝ ልቤ እየበገነ
አሁን ያልኩት ነገር ደህንነት ከሆነ
አዎ እኔ ደህና ነኝ!
https://t.me/poem_by_poem
2.1K viewsbelaya, 12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 18:48:37 by B.A

ብዙ ብር አውጥቼ የገዛሁት ዘይት
ብሩን ሳሰላስል ተደፋ በድንገት
እናም ወዳጆቼ እናም ወገኖቼ
ልሞት ስለሆነ በገመድ ገብቼ
ሞተልሽ ብላችሁ ለሚስቴ ንገሯት
ከዘይቱ ይልቅ
የእኔ ሞት ነው እና ለእርሷ የሚቀላት
goodby
https://t.me/poem_by_poem
449 viewsbelaya, 15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 18:28:57
እቺን ውብ እዬልኝ መልኳን ሳይ ከማንሳት አልተቆጠብኩም ውበቷ ማርኮኝ

@geez_mulat
"በመንገዴ ምንጣፍ "
498 viewsጥ ቁር ዝምታ, 15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ