Get Mystery Box with random crypto!

ሲባል እሰማለሁ 'ህይወትን አሸንፍ' መኖር አይበልጥም ወይ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ሲባል እሰማለሁ
"ህይወትን አሸንፍ"
መኖር አይበልጥም ወይ
ከመወዳደር ጽንፍ?

እንደሆን ነው እንጂ
የልቡን መቃብር በሳቅ የከለለ
ህይወት ስትሸነፍ ያየ ሰው የት አለ?

ምንደነው መሸነፍ?
ማንን ነው ማሸነፍ ?

ለይመሰል ነው እንጂ እንዲያው ተዘክሮ
መች ይወዳደራል ነዋሪና ኑሮ?

ወዴት ነው መድረሻ የት ነው መነሻዬ?
:
መኖር አይደለም ወይ የመኖር ድርሻዬ?

ሀገሬው መረሬው
"ቀንህን ብለጠው" ብሎ ይለፍፋል
እውነት በሰው አቅም ህይወት ይሸነፋል?

ኤልያስ ሽታኹን https://t.me/poem_by_poem