Get Mystery Box with random crypto!

ግን እወድሻለሁ ---------------------- እንዳይከፋሽ ውዴ... ናፍቄሀለሁ ወይ? ብለሽ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ግን እወድሻለሁ
----------------------
እንዳይከፋሽ ውዴ...

ናፍቄሀለሁ ወይ? ብለሽ ያልሽኝ ለታ
ራሴ ናፍቆኛል
ብየ ነው የምልሽ ያላንዳች ይሉኝታ

ትወደኛለህ ወይ? ብለሽ ያልሽኝ ጊዜ
እኔን እወዳለሁ
ብየ ነው የምልሽ ያላንዳች ትካዜ

ታምነኛለህ እንዴ? ብለሽ ከጠየቅሽኝ
እራሴን አምናለሁ
ብየ ነው የምልሽ ምንም ቅር ሳይለኝ

እንዳይከፋሽ ውዴ...
ላንች ስትጠይቂኝ ለእኔ የምመልስ
ቀውሼ አደለም ወይም አጥቼ መልስ
ምክንያቱ ይሄ ነው

አጥንቴ ካጥንትሽ
ደምሽ ከደሜ ጋር ስለተዋሀደ
ይህ ሚስኪን መንፈሴ
አንችን አይጠላሽም እኔን ከወደደ!!!

By belaya

https://t.me/poem_by_poem