Get Mystery Box with random crypto!

እስቲ አሁን ደግሞ የዮሮናን ቤተሰቦች እናስተዋውቃችሁ። እናቱ ቅናት ትባላለች። የብርድ በሽታ አለ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

እስቲ አሁን ደግሞ የዮሮናን ቤተሰቦች እናስተዋውቃችሁ።

እናቱ ቅናት ትባላለች። የብርድ በሽታ አለባት ፤ ቁርጥማት ያሰቃያታል በተለይ የግራ እጇና እግሯ ለ ብርድ በሽታ የተጋለጠ ነው ።



እህቱ ደግሞ ማስቀናት ትባላለች።


አባቱ ደግሞ አባ ኩራት ይባላሉ፤ እዚህ ዓለም ላይ ከክብራቸው የሚበልጥባቸው ነገር የለም።

ማስቀናት ሰዎች እንዲቀኑባት ትፈልጋለች ፤ ብትቸገር ዕንኳን ተቸግሬያለሁ አትልም።

ምሬትን አታውቅም፤ ሁልጊዜ ስል ጥሩ ጎኗ ዕና ስለተመቻቸ ኑሮዋ ነው የምታወራው።


ፌስቡክ ላይ አሪፍ አሪፍ እየለበሰች፤ ዓሪፍ ዓሪፍ ዕየተመገበች መፖሰት ያስደስታታል።


መዝናኛ ቦታዎች ሄዳ ፎቶ ካልተነሳች፤ የተዝናናች አይመስላት።( የተነሳቻቸውን ፎቶዎች ለ ጓደኞቿ በማሳየት ለማስቀናት)

በዚህም ምክንያት ጓደኞቿ ስለሚቀኑባት አይወዷትም።