Get Mystery Box with random crypto!

አዎ እኔ ደህና ነኝ አዎ እኔ ደህና ነኝ፣ ብቻ ዝም ብሎ እራሴን ያመኛል የወገኔ ስ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

አዎ እኔ ደህና ነኝ

አዎ እኔ ደህና ነኝ፣
ብቻ ዝም ብሎ እራሴን ያመኛል
የወገኔ ስቃይ፣
አንቅልፍ እየነሳ ይቀሰቅሰኛል!
አዎ እኔ ደህና ነኝ፣
ሽብር አናውዞታል የልቤን ከተማ
ሰው በሞተ ቁጠር፣
ደረት እየደቃሁ አበራለሁ ሻማ!
አዎ እኔ ደህናነኝ፣
እብደት ተጠግቶኝ ዝም ብዬ ስቃለሁ
ሀገሬ ቁጭ ብዬ፣
ልክ እንደ ባይተዋር ሀገር ናፍቃለሁ!
አዎ እኔ ደህና ነኝ፣
ወገኔ ባልኩት ሰው ዘመኔን ምጉላላ
ሆዴን እየራበው፣
በቀን ሀያ ግዜ መከራ ምበላ!
እናም፣
ሀዘን አሰቃይቶኝ ልቤ እየበገነ
አሁን ያልኩት ነገር ደህንነት ከሆነ
አዎ እኔ ደህና ነኝ!
https://t.me/poem_by_poem