Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የሰርጥ አድራሻ: @gitmnamuzika
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.30K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብበት ቻናል ነው ይከታተሉ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ ሚክስ ከፌሊኖቫ ጋር
Creator@fellynovaa
Invite link to share
https://t.me/ vKDN0lXKiKFmN2M0

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-03-21 18:50:11 -

ሻሽ ወገብ በሌለው ማደሪያ ቤት ያለች፣
የሆነች አራስ ሴት ጭቃ ላይ ቁማለች፣

ወይ ወልዳ አልፀደቀች ፣
ወይ መክና አልሞተች፣
እንዲሁ በባዶ ኢትዬጵያን መስላለች፣
_
ግዕዝ ሙላት

@geez_mulat
473 viewsጥ ቁር ዝምታ, 15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 10:29:08
ሰው የልማድ ውጤት ነው
ዓለም የልማድ ውጤት እንደሆነችው ሁሉ በልማድ እናጣት ዘንድ የተሰጠችን የልማድ ልምድ ነች !

ሰው ልማድ ነው!
መሬት የልማድ ምኩራብ ናት! ሰማይ የዓይን የሰመመን ልማድ ነው!

"ሁሉም ነውሮች መጥፎ ነገሮች በሙሉ የልማድ ውጤት ይሆኑ ዘንድ ነው!"

መልካም ነገሮች ፈጥረን የለመድናቸው ሳይሆኑ ከመልካሙ ዓለም ስለመልካም እንድንለምዳቸው የተገበሩልን ግሩም ሎሌዎች ናቸው

ምንም ነገር ራሱ በምንም የልማድ ሀቅ ነው

"ሰው የልማድ ውጤት ነው !!!!"

@geez_mulat

ግዕዝ ሙላት
755 viewsጥ ቁር ዝምታ, 07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 15:07:00

በማላውቀው ሀገር
ጥሎኚ የማውቀው ሰው ፣

መንገዴን በሙሉ
የውሃ ኑሮ አረገው፣

____
@geez_mulat
@geez_mulat

ግዕዝ ሙላት
555 viewsጥ ቁር ዝምታ, edited  12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 13:49:41 እንባ የለሽ ህንፃ
ወዝ አፍሳሽ እዳ፣
ሊሞት ሲል ሆነ እጂ
ሰው ነፍስን ሚረዳ፣


-____
@geez_mulat
@geez_mulat

ግዕዝ ሙላት
647 viewsጥ ቁር ዝምታ, edited  10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 06:16:23 ርዕስ የሌለው
እናት ህይወት ናት የሌላት መጨረሻ
በሀዘን በደስታ የምትሆን መሸሻ
ምንዳ ናት ሁልጊዜ ለልጇ መከታ
ልጇን ታድናለች ህይወቷን ሰውታ
ደስታሽ ምንድነው ንገሪኝ እናቴ
አድርግልኝ ብለሽ እዘዢኝ በሞቴ
የት ቦታ ልውሰድሽ ወዴትኛው ገዳም
ዘብር ? ላሊበላ ? ወይስ ግሸን ማርያም ?
ቁልቢ ገብርኤል መርጦለማርያም ?
ሸንኮራ ዮሐንስ አጃና ሚካኤል?
ንገሪኝ እማዬ ደስታሽን ልካፈል
ከየገዳሙ ደጅ ደርሰን እንሳለም
ቆመን እናስቀድስ መስቀሉን እንሳም
ለፅላቱ እንስገድ ለነድያን እንመፅውት
እንጠጣ ጠበሉን እንቀባ እምነት
እባክሽ ንገሪኝ የፈገግታሽን ምንጭ
ምኞትሽ ምንድነው የደስታሽ ፍንጭ
ስኬት ነው ያልሺውን ሁሉንም ንገሪኝ
እባክሽ እናቴ እኔንም ተረጂኝ
አሁን አድጌአለሁ ለኔ አትጨነቂ
ማየት ፈልጋለሁ አንቺ ስትስቂ
ያኔ...ያኔ ልጅ እያለሁ ስስቅ ስትደሰች ሳለቅስ ስታዝኝ
ራበው ጠማው ብለሽ ስትንከባከብኝ
ለዚህ ደረስኩልሽ ባንቺ ትልቅ ልፋት
ወደፊቴን ደሞ አስቢኝ በፀሎት



∞∞∞∞∞እናቴ እወድሻለሁ። ∞∞∞
189 viewsŦıņ§ĥų ¥ěĥűªľą§ĥ€ŧ, 03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 21:48:54
____

አንዳንድ ከንፈር አለ ፥
ማር የሚመስል፣
ለስላሳ እሚመስል፣

የሂዎት እሬትን ፥
ደብቆ ሚያበስል ፣
ደብቆ ሚቆስል፣


___
ግዕዝ ሙላት

@geez_mulat
537 viewsጥ ቁር ዝምታ, 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 17:15:57 ____

አንዳንድ ሰላም አለ ዝምታን ሚፈራ፣

ራሱን ደብቆ በጩኸት ሚሰራ፣

___
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat
767 viewsጥ ቁር ዝምታ, 14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 17:32:09 አያ ሙሌ
____

አያ ሙሌን መስዬ
ቅርፅ ጥን ስሰራ፣
ሙሉጌታን ይመስል
ከሀሳቦች ጋራ ፣
ሁኜ ባላጋራ፥
ከራሴ ስዳራ ፣
ማንም ሳይረዳው
ከዘመኔ በሯል የፊደሌ ቁራ፣

እፅፍለው እኔ፣ ብዕርን አምኜ፣
ከዘመን ቀድሞ፥ የፃፍኩት ስንኜ፣
ይረዱትስ ይሆን ከትናንቱ ሁኜ
ትውልድ ይዘክረው ፥እኔ ሞት ላይ ሆኜ፣

እንጃ እሆን_ ይሆን አያሙሌ፣
ለማትነሳ ጥበብ
በስጋ መረገጥ ይሆናል እድሌ ፣

እያልኩኚ በውኔ፣
ስንኚ እቀርፃለው
ፊቱን ሳዬው በአይኔ ፣
____

መታሰቢያነቱ:_

ለባለቅኔው :ሙልጌታ ተስፍዬ (አያ ሙሌ)
( ሳይነሳ ለወደቀው )

---
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat
391 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 23:30:46 #አባ_ከና(#aba_kana)
በፍቅርሽ ስንገላታ ሳትዪኝ አባ ከና፣
ዘንድሮ ደረሰ አለፈና አምና።
አፍንጫሽ ስር ሆኜ ሳትቆጥሪኝ ከቁብ፣
ዘመን ተሻገረ ያ ጊዜ እፁብ።
ባለቤት አልባ ተጥዬ ከኩሲ፣
ልቤ እየናፈቀው መቀመጫ ኩርሲ።
እንዴት አስቻለሽ ሰጠሽ ፅናት፣
እንዲህ አልነበርኩም ስታውቂኝ ትላንት።
መውደድሽ ነው እንዳልሽር ያንኮታኮተኝ፣
በስሜት አንፆ በግርማ እንዳልኮተኮተኝ።
ምን ብትጠጪ አንጀትሽ የደነደነው፣
በቸልታሽ ቆረቆዘ በማፍቀርሽ የዳነው።
#Makoniin_Yooseef
344 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 20:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 09:42:53 ከእለታት ሁለት ቀን ከ "ለ"እስከ "በ" ====================== በመጀመሪያው ቀን እቤት እንደገባሁ ወንድ ልጅ ነኝ እና ተደብቄ አነባሁ አይሆኑትን ሆኜ ያ ሌሊት ቢነጋ ወጣሁኝ ከቤቴ መውደዴን ፍለጋ ፈልጌ ፈልጌ እግሬን ድክም ሲለኝ ስልኳን እንደሰጠችኝ ያን ጊዜ ትዝ አለኝ ባላወቅሁት ቅፅበት ስልኬን አወጣሁኝ ድምፁን loud አድርጌ በፍጥነት ደወልኩኝ…
627 viewsbelaya, edited  06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ