Get Mystery Box with random crypto!

ርዕስ የሌለው እናት ህይወት ናት የሌላት መጨረሻ በሀዘን በደስታ የምትሆን መሸሻ ምንዳ ናት ሁ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ርዕስ የሌለው
እናት ህይወት ናት የሌላት መጨረሻ
በሀዘን በደስታ የምትሆን መሸሻ
ምንዳ ናት ሁልጊዜ ለልጇ መከታ
ልጇን ታድናለች ህይወቷን ሰውታ
ደስታሽ ምንድነው ንገሪኝ እናቴ
አድርግልኝ ብለሽ እዘዢኝ በሞቴ
የት ቦታ ልውሰድሽ ወዴትኛው ገዳም
ዘብር ? ላሊበላ ? ወይስ ግሸን ማርያም ?
ቁልቢ ገብርኤል መርጦለማርያም ?
ሸንኮራ ዮሐንስ አጃና ሚካኤል?
ንገሪኝ እማዬ ደስታሽን ልካፈል
ከየገዳሙ ደጅ ደርሰን እንሳለም
ቆመን እናስቀድስ መስቀሉን እንሳም
ለፅላቱ እንስገድ ለነድያን እንመፅውት
እንጠጣ ጠበሉን እንቀባ እምነት
እባክሽ ንገሪኝ የፈገግታሽን ምንጭ
ምኞትሽ ምንድነው የደስታሽ ፍንጭ
ስኬት ነው ያልሺውን ሁሉንም ንገሪኝ
እባክሽ እናቴ እኔንም ተረጂኝ
አሁን አድጌአለሁ ለኔ አትጨነቂ
ማየት ፈልጋለሁ አንቺ ስትስቂ
ያኔ...ያኔ ልጅ እያለሁ ስስቅ ስትደሰች ሳለቅስ ስታዝኝ
ራበው ጠማው ብለሽ ስትንከባከብኝ
ለዚህ ደረስኩልሽ ባንቺ ትልቅ ልፋት
ወደፊቴን ደሞ አስቢኝ በፀሎት



∞∞∞∞∞እናቴ እወድሻለሁ። ∞∞∞