Get Mystery Box with random crypto!

#አባ_ከና(#aba_kana) በፍቅርሽ ስንገላታ ሳትዪኝ አባ ከና፣ ዘንድሮ ደረሰ አለፈና አምና። አ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

#አባ_ከና(#aba_kana)
በፍቅርሽ ስንገላታ ሳትዪኝ አባ ከና፣
ዘንድሮ ደረሰ አለፈና አምና።
አፍንጫሽ ስር ሆኜ ሳትቆጥሪኝ ከቁብ፣
ዘመን ተሻገረ ያ ጊዜ እፁብ።
ባለቤት አልባ ተጥዬ ከኩሲ፣
ልቤ እየናፈቀው መቀመጫ ኩርሲ።
እንዴት አስቻለሽ ሰጠሽ ፅናት፣
እንዲህ አልነበርኩም ስታውቂኝ ትላንት።
መውደድሽ ነው እንዳልሽር ያንኮታኮተኝ፣
በስሜት አንፆ በግርማ እንዳልኮተኮተኝ።
ምን ብትጠጪ አንጀትሽ የደነደነው፣
በቸልታሽ ቆረቆዘ በማፍቀርሽ የዳነው።
#Makoniin_Yooseef