Get Mystery Box with random crypto!

አያ ሙሌ ____ አያ ሙሌን መስዬ ቅርፅ ጥን ስሰራ፣ ሙሉጌታን ይመስል ከሀሳቦች ጋራ ፣ ሁኜ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

አያ ሙሌ
____

አያ ሙሌን መስዬ
ቅርፅ ጥን ስሰራ፣
ሙሉጌታን ይመስል
ከሀሳቦች ጋራ ፣
ሁኜ ባላጋራ፥
ከራሴ ስዳራ ፣
ማንም ሳይረዳው
ከዘመኔ በሯል የፊደሌ ቁራ፣

እፅፍለው እኔ፣ ብዕርን አምኜ፣
ከዘመን ቀድሞ፥ የፃፍኩት ስንኜ፣
ይረዱትስ ይሆን ከትናንቱ ሁኜ
ትውልድ ይዘክረው ፥እኔ ሞት ላይ ሆኜ፣

እንጃ እሆን_ ይሆን አያሙሌ፣
ለማትነሳ ጥበብ
በስጋ መረገጥ ይሆናል እድሌ ፣

እያልኩኚ በውኔ፣
ስንኚ እቀርፃለው
ፊቱን ሳዬው በአይኔ ፣
____

መታሰቢያነቱ:_

ለባለቅኔው :ሙልጌታ ተስፍዬ (አያ ሙሌ)
( ሳይነሳ ለወደቀው )

---
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat