Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የሰርጥ አድራሻ: @gitmnamuzika
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.30K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብበት ቻናል ነው ይከታተሉ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ ሚክስ ከፌሊኖቫ ጋር
Creator@fellynovaa
Invite link to share
https://t.me/ vKDN0lXKiKFmN2M0

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-02-08 11:36:32 ልፅፍልሽ ነበር በቀለም አድምቄ
ልፅፍልሽ ነበር ብራናየን ስየ ፊደላት አጥብቄ
ልፅፍልሽ ነበር ያለችሎታየ ውስጤን አስጨንቄ
ግና ምን ያደርጋል አንችን የሚመጥን ቃላት አጣሁልሽ
አፌ ተያያዘ ኮልታፋ ሆንኩልሽ
ጣቶቸም ራዱ ሰባራ ሆኑልሽ።
Hawlet Ali
404 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, edited  08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 11:36:31 ትቻለሁ ስላንቺ  
መስሎኝ ምታፈቅሪኝ
        ተሳስተሽ ማትዋሺኝ
ልብሽን ደብቀሽ
           ከንፈርሽ ሰጠሽኝ
እኔም ተታልዬ
          ፍቅርሽ እውነት መስሎኝ
ጥበብ ባጠራኝም
           ገጣሚ ሆኛለሁ የማገኝሽ መስሎኝ

አሁንማ ውዴ
           ሁሉም ሳይሆን ቀረ
መግጠሙም ይቅርብኝ
                  አንቺን ካልቀየረ
ትቻለሁ ከንግዲህ
          ህልሜ መና ቀረ
አንቺም ገደል
          ግቢ መሞቴ እስካልቀረ
ጥበብ ባጠራኝም እጋፈጣታለሁ
397 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, edited  08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 11:36:31 ትናንት ዛሬ ቢሆን
ዓለም ወደ ኋላ ብትዞር

በምስራቅ ብትገባ የወትሮዋን ትታ
ቢቀየር ተመኘሁ የፀሀይ ዙረቷ

የትናንቱ ጭልምት በነበረ ንጋት
ስንቱን ባበረርኩት
አያሌውን ደሞ ከመንጎድ 
                   ባስቆምኩት          
ማርፈዴን እራሱ ምነው   
               ባስረፈድኩት።
347 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, edited  08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 02:53:43 በስተ_ኋላ


ስትሆኚ ፍም እሳት እንደተቆጣ ገላ፣
አንዳዳሪ ጠቢብ በአፍ ብቻ የጠላ፣

ጠላ እየበረዙ ዳሩን ጋር መዘመር፣
የዘንድሮ ብጥብጥ አይሎ መቸገር፣
አሁንማ አዬሁት
ሰው ለአገር አይኖርም ከዘሩ በስተቀር ፣


# ግዕዝ ሙላት
648 viewsOne, edited  23:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 13:28:41

668 viewsOne, 10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 13:28:27

681 viewsOne, 10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 12:16:15 ====///===
አንዳንድ ሳዉ አሌ
አይኑና ልቡ የተንሸዋሬ
በዉሸት አንደበት
ቃላት አሳምሮ
ፍቅር እየዘመሬ
ያለ ርህራሄ
ስንት ፍቅር ገድሎ
ስንት ልብ ሰበሬ
====//=====
By Gutu.Z
766 views༺ Gutu.Z ༻, 09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 23:15:38 አጫሽ ሴት እፈልጋለው


part 1

ገጣሚ ግዕዝ ሙላት
1.1K viewsOne, 20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 19:19:29 ማህተማ ጋንዲ - ሰለ ለውጥ ከተናገሩት በጥቂቱ፦

"በዓለም ላይ ማየት የምትፈልጉትን ለውጥ በራሳቹ አድርጉት።"

"የራሳችሁ ለውጥና ሥልጣን በእጃችሁ ነው።"

"ራሳችንን መቀየር ከቻልን የመላው ዓለም ይቀየራል።"

"የራስን ስሜት መቆጣጠር አለመቻል አቅጣጫ ጠቋሚ በሌለው መርከብ እንደመጓዝ ነው።"
1.3K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, edited  16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 19:19:29 ማርከስ ቱሊስ ሲሴሪዮ የተባለው ጣሊያናዊ ጸሐፊ እና ፈላስፋ፣ “መጻሕፍት የሌለዉ ቤት እና ነፍስ የሌለዉ የሰዉ ፍጥረት አንድ ናቸዉ” ብሏል። ጸሐፊው፣ መጽሐፍ ለሰው ልጅ ከኦክስጅን የማይተናነስ ግልጋሎት እንደሚሰጥ የገለጸበት አባባል ነው።

ማንበብ፤

▸ የተሻለ አስተሳሰበብ ባለቤት ያደርጋል
▸ ጠያቂ ያደርጋል
▸ ተመራማሪ ያደርጋል
▸ የአስተሳሰብን አድማስ ያሰፋል
▸ በሥነ ምግባር መታነጽን ያድላል
▸ የሌሎችን ስሜት የመጋራትን እና አዛኝ የመሆን ስብዕና ባለቤት ያደርጋል
▸ ለችግሮች መፍትሔ ሰጪ ያደርጋል
▸ የፈጠራ አቅምን ያሳድጋል
▸ የተግባቦት ክህሎትን ያዳብራል
▸ በራስ መተማመንን ያሳድጋል
▸ ሐሳቦች ኹሉ ትክክል ናቸዉ ከማለት ያድናል
▸ ውጥረትን ይቀንሳል
▸ ትውስታችንን ያጎለምሳል
▸ የመፃፍ ክህሎታችንን ይጨምራል
▸ የቃላት ክምችትን ይጨምራል
1.3K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, edited  16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ