Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የሰርጥ አድራሻ: @gitmnamuzika
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.30K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብበት ቻናል ነው ይከታተሉ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ ሚክስ ከፌሊኖቫ ጋር
Creator@fellynovaa
Invite link to share
https://t.me/ vKDN0lXKiKFmN2M0

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2023-02-06 09:36:57 -_-_--_-
የበጋ ስም
-_-_-_-_-_-_-_

ጭራ ጭራ አድራ ፣
አፈሩን አውጣ ቆፋፍራ ዋለች ከአፈር ስትዳራ፣
ጥጉን ጎን አለቺው ጭቃ ነፍስ መስጥራ፣

እሷ በሏት የዋህ
እኔን በሉኝ ብልጥ፣
ማን ሌሊት ተመኜ በጠሃይ መናጥ
ማን ፈልጎ ወዛ
ማን አሰበ መሮጥ፣
በጫርሽው ሚቀበር በቆፈርሽው ሚዋጥ፣

እኔን አሉኝ ገዳይ አንቺን አሉ ሟቺ
ማን በቆፈረው ወዝ
ሲታለብስ ያድራል በጋኔላም ምቺ፣

አዎ: ለካ አንቺ የዋህ ነሽ፣
በጋ አለም ሳታውቂ በክረምት የቆፈርሽ፣
ሸርተት ሸርተት ሲል
ዝናቡ ሲነጥፍ እንደገደል አፈር፣
እውነትም የዋህ ነሽ ወዬው አለማፈር፣
በበጋ ገለሺ በክረምት መቆፈር፣

_-_--_-__

ግዕዝ ሙላት
1.3K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 09:36:57
1.0K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 09:36:57 _-----__

ጭርት ያሳመፀው መአት
በመርዜ ስፈታት ፣
በዲዛ እንሶስላ አልሆን ሲለው መብዛት፣

አሞራ በሳመው ወዜ ፣
ዘመን ቀን አይቶ ከጭልፊት አፍ ፍትህ ያዘ ጊዜ፣
እርግብ ሲከበክብ በወደቀ እህል ቁራ ሆነ ልቤ፣

ከተወለድኩ ኋላ ለመጣ አርምሞት፣
ከመሞቴ በፊት ለሚመጣ መሞት
ጭርት ከአፍ ሲሆን ይዘበናል ( አ)መት፣
ይምጣ እጂ የእመት ( ዓ)መት፣

ዛፍ ሊወርሱ አንካሳ ቁራ ቢያዘምቱ
ባዶ አሞራ ሆነ በየ'ዲዛው ቤት ቢዘምቱ ቢዘምቱ፣
__
( ዲዛ )
____
ግዕዝ ሙላት
1.0K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 11:18:08 እኔ እና ሚስቴ(ከ "ሀ" እስከ"ፐ") ==================== ከእለታት በአንድ ቀን...(ከ "ሀ" -"ሃ") እረፍት ስለፈለኩ ከአልጋየ ተጋደምኩ ግና ምን ያደርጋል ቀኝ አይኔን ሸከከኝ ግራ ጎኔን ወጋኝ ከአልጋየ ወርጄ ከቤቴ ወጣሁኝ መንገድ ዳር ቁጭ ብየ በሀሳብ ነጎድኩኝ የወጋኝን ጎኔን በእጄ…
806 viewsbelaya, edited  08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 22:36:51 #ሲበሉ_አድርሰኝ
አይ የሀገሬ ሰው ሆዳሙ÷
ከርሱ እኮ ነው ገዳሙ።
ከቶ ለሚተፋው ገብቶ የመነነ÷
እንደ ሃበሻ ማናለ የገነነ።
ሲወጣ ፀልዮ ሲበሉ አድርሰኝ÷
ከገበታው ዙሪያ ወሰደህ አንግሰኝ።
ሲጣሉ መልሰኝ ጠፍቶ አስታራቂ÷
እንትፍ ባይ ባርኮ መራቂ።
ያሳጣ ለአዛውንት መቀመጫ ኩርሲ÷
ሁሉም እየተሾመ ለፍቅር ከይሲ።
ትውልዱን ነስቶት ጭራያዥ ሸምጋይ÷
ስንቱ እውቀት አሞቀ ድንጋይ።
#በማክቤል
#plz_share
595 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 22:36:51 #አህያ_ከአመዱ
በዚህች ብሄርተኛ የአያት ሀገር፣
ዘመድ ከዘመዱ ተብሎ ሲነገር።
ጎሳህን አስቀድም ነው ትርጉሙ፣
የወንዝ ልጅ ስለሆነ ደሙ።
ደግሞ እኮ በአህያ ያድበሰብዋል፣
ፍም አመዱን ለክምር ያግበሰብሰዋል።
ጠብደሉ እንስሳ ጀርባው በማበዱ፣
መታከክን ቢመረጥ ለእፎይታ መንገዱ።
ተረፈ ለሰው ዘር ትስስር፣
ግንድነትን ትቶ መጣላት በስር።
ቢገባው ከስጋው የቅርብ ጎረቤቱ፣
ራስ ነበር አፍ አንደበቱ።
የብዕር ስም:#ማክቤል
plz share
594 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 22:36:51 #ጨረቃ_ላይ
እመ ብርሀን እንዳረፈችበት ዙፋን፣
እንደ መጥምቀ መለኮት ምስለ ሽፋን።
ጨረቃ ላይ በህቡዕ ተስለሻል፣
ታዲያ ቆንጆ ለመባል ምን ያንስሻል።
መስመሮች በጠፉት ልሙጥ ዝርጋታ፣
ክዋክብት ሲመልሱ የልብን እርጋታ።
በማቅለሚያው ጩኸት በስሱ እርሳስ፣
ዝምታን የሚያዜም የፍቅር ለሆሳስ።
በነጥቦች መሀል ወሰኑ ያረገሽ፣
የእስትንፋሱ ደጃፍ በገፍ የማገሽ።
ከድፍርስ ሰማይ በታች በአራዊት ሜዳ፣
ዛሬም ወይዘሪት ነሽ ለመውደድ ሰሌዳ።
የብዕር ስም:#ማክቤል
ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ያድርጉ!!!
551 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 11:01:34 መታመን ሞቷል መታመን ሞቷል              ቀበርኩት ብቻዬን               ትናንትና ማታ አፍስሼው እምባዬን                  ልቤ እየሳሳለት                  ሆዴ እየራራለት ትናንት እሁድ ለታ ሸኘሁት በማታ አንቺ ና ብለሺኝ ጥለሺኝ ስትጠፊ             …
1.3K viewsbelaya, 08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 10:19:25
መታመን ሞቷል



መታመን ሞቷል
             ቀበርኩት ብቻዬን

              ትናንትና ማታ
አፍስሼው እምባዬን

                 ልቤ እየሳሳለት
                 ሆዴ እየራራለት

ትናንት እሁድ ለታ
ሸኘሁት በማታ

አንቺ ና ብለሺኝ
ጥለሺኝ ስትጠፊ

             የገላዬን ሙቀት
             ወደዛ ስትገፊ

              ብከብደኝም ቅሉ
              ጨከነና ልቤ

የመቃብር ወጉን
ስዬው በምናቤ

እምነትን ቀበርኩት
ሸኘሁት ባሳቤ


by Gutu.Z
1.3K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 00:56:02 #ጨረቃ_ላይ
እመ ብርሀን እንዳረፈችበት ዙፋን፣
እንደ መጥምቀ መለኮት ምስለ ሽፋን።
ጨረቃ ላይ በህቡዕ ተስለሻል፣
ታዲያ ቆንጆ ለመባል ምን ያንስሻል።
መስመሮች በጠፉት ልሙጥ ዝርጋታ፣
ክዋክብት ሲመልሱ የልብን እርጋታ።
በማቅለሚያው ጩኸት በስሱ እርሳስ፣
ዝምታን የሚያዜም የፍቅር ለሆሳስ።
በነጥቦች መሀል ወሰኑ ያረገሽ፣
የእስትንፋሱ ደጃፍ በገፍ የማገሽ።
ከድፍርስ ሰማይ በታች በአራዊት ሜዳ፣
ዛሬም ወይዘሪት ነሽ ለመውደድ ሰሌዳ።
የብዕር ስም:#ማክቤል
ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ያድርጉ!!!
1.4K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 21:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ