Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የሰርጥ አድራሻ: @gitmnamuzika
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.30K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብበት ቻናል ነው ይከታተሉ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ ሚክስ ከፌሊኖቫ ጋር
Creator@fellynovaa
Invite link to share
https://t.me/ vKDN0lXKiKFmN2M0

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-02-22 16:29:18 #ኖር
ተቀበይ እንግዳሽ ነኝ በኖር፣
ከልብሽ ጠልቄ በተድላ እንድኖር።
ከኩራትሽ ወንበር ትንሽ ተነሺ፣
የምታድሪው አይደለም ጤና ስትነሺ።
እኔም እመልሳለሁ በእግዜር ሰላምታ፣
እንድትሰነብት መንፈሴ ከነፍስሽ ተስማምታ።
ብቻ እንዳይቆየኝ በርሽ ተጠርቅሞ፣
ደጅ መጥናት አልፈልግም ቆሞ።
ለምን ሳይወልቅ የአያትሽ ባርኔጣ፣
እንዴት ሳይታጠፍ የሚያነቡት ጋዜጣ፣
የወደፊት ባልሽ ከቤታቸው ስመጣ።
ባይተዋርነት ተሰማኝ ፀጉረ ልውጥነት፣
የሰው ልጅ ባህሪ ሲስት ወጥነት።
#መኮንን_ዮሴፍ(ባቢ)
348 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:29:18 #ትኮፈስ
እንድታነጅብ ተጀንና ብላችሁ ትኮፈስ፣
ለምን የምትሞሏት የጉራ መንፈስ።
ላይጠቅማችሁ ነገር በሰው ብትገመት፣
እረፉ ባካችሁ በታምሪያለሽ መዝመት።
መኮንን ዮሴፍ
350 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:29:18 ቅቤ ቀቢዎቹ
ቅቤ ይመስል ደም እየቀቡሽ፣
ከፊትሽ ወዘና ቀድተው አገረጡሽ።
ሙት ተጥሎበት ቀዬሽ በከተ፣
ማስረሻ ልጅሽም ስንዝር አልመከተ።
በል አስረሴ አርዳት ሌሊትም አይደለ፣
የአብራኳ ክፋይ ቁልቁል እንደተገደለ።
ያን ግንበኛ ቤቱን ቀይ የለቀለቀ፣
በመዝገብ በችሎት እንዲያስጠይቀው ያላወቀ።
ሸሚዙ ቀለም ነክቶት ቢያዩ፣
አሻራ ፍለጋ ሳምንት ተወያዩ፣
ከገዳይ ጋር ባርኔጣ ነስተው ተለያዩ።
ሀገሬ ድንጋይሽ መንገድ ዘጋ፣
ትውልድሽ በሙሉ ሆ ብሎ አዛጋ።
344 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:29:18 #ጽጌሬዳ_ለብሰሽ
አበባይቱ ፍቅሬ ከቀጠሮው ቦታ፣
ጽጌሬዳ ለብሰሽ ነይ የመውደድን ኩታ።
ከቀለም መርጠሽ የደመቀ ቀይ፣
በይፋ አወጀሽ የሱ ነኝ በይ።
እኔም ጠብቅሻለሁ በቢራቢሮ ከረቫት፣
አንገቴን አስሬ ልቤንም ስፈታት።
ከመክተሚያችን ብታዪ ቄስ የጠመጠመ፣
አትስጊ ግቢ ነው ሊያስተሳስረን የተሾመ።
#መኮንን_ዮሴፍ(ባቢ)
256 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:29:18 #አንድ_ያጣላል
በእዛ በማዕዱ በፍቅር ገበታ፣
አጉራሽ መርህ አለው መንታ።
አንድ ያጣላል ብዬ ብደግማት፣
ጉሮሮዋ ጠቦ የአሳ እሾህ አነቃት።
ያልሽኝ በከንቱ ሁለት ያፋቅር፣
ለምን ሆነና ቧጦ ባያቅር።
ለፆመኛ ዳገት ደሙን አቀዝቅዞ፣
ልውረድ ልውረድ ይላል እንጥል አመርቅዞ።
አይ እማ ብትገላግያት ተቆርጦ፣
አፎይ ማለት እንጂ ቁስል ተፍረጥርጦ።
አትፍሪ ክስ ካለፈውስ አካሚ፣
በሽታውን ያውቃል የተጋጨውን ታማሚ።
መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)
241 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:29:17 #የእሳት_ራት
በኩራዝ መካከል ከንፈሽ ስትርገበገቢ፣
ገምቼ ነበረ ከድጥ እንድትገቢ።
ልትሆኚ መሄድሽ የእሳት ራት፣
ደ'ሞ ምን ሊፈይድ ከነበልባል መዳራት።
ዘው ለማለቱ አትይም ይፋጃል፣
ማን ከጋመ ቧልት ይቀለምዳል።
የቀን ጎዶሎ ሲያሮጥ ያመጣሽ፣
በሻማ ውሃ ቀቅሎ ቀጣሽ።
ጓድሽም እንዲያው ናት ያንቺ ዘመድ፣
ማሰሪያ ሳታበጅ ገምጅታ ማጥመድ።
ፍቅሬ አዘንኩለት የዳሰስሁት ገላ፣
በክሩ ሰደድ ተጨምቆ ሲበላ።
#መኮን_ዮሴፍ(ባቢ)
237 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:29:17 #ስም_ያለው
ያኔ በፍቅራችን ድንቁ ጊዜ፣
ሳይለቀን በፊት የቁልምጫ አባዜ።
ሞክሼን ስትጠሪው አቤት ብዬ ነበር፣
ስም ያለው ሞኝ ነው ሲደናበር።
ሞረሽን ስትፈልጊ ወዬ እልሻለሁ፣
እኔን እየመሰለኝ ቀልቤን እገብርልሻለሁ።
ዛሬስ ልቀይረው መባሌ ካለቀረ፣
የሴጣን ጎረቤት ለመልሴ ካቃረ።
አልበጀኝምና ለወጥኩት እንግዲህ እናኔ፣
አንቺ ነሽ ምታወቂው የህይወት ምናኔ።
አውጪልኝ ባክሽ አጣሁኝ ምትክ፣
ንሰሐ አባቴ አይስሙ ለራሴ ብርክርክ።
#መኮንን_ዮሴፍ(ባቢ)
232 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 16:27:57 ህይወታችን ላይ ትልቅ በጎ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ 10 አመለካከቶች!

1. ራሴን ለመውደድና ለመቀበል ሰዎች እስኪወዱኝና እስኪቀበሉኝ አልጠብቅም።

2. ትክክለኛውን ነገር አደርጋለሁ እንጂ ሰዎችን ሁሉ ለማስደሰት አልሞክርም።

3. ትችቶች እንዲያስተምሩኝ እንጂ እንዲሰብሩኝ አልፈቅድም።

4. እኔ በስህተቶቼ define አልደረገም።

5. ስህተቶቼን ከስኬቶቼ በላይ አግዝፌ አላይም።

6. ሰዎች ሁሉ እንደኔ እንዲያስቡ አልጠብቅም።

7. የማልቀይራቸውን ሀቆች እቀበላለሁ።

8. ሰዎች እንዲያማክሩኝ እንጂ እንዲወስኑልኝ አልፈቅድም።

9. በማልቀይረው ትላንት ላይ ሳይሆን ባለኝ ዛሬ ላይ አተኩራለሁ ።

10. ደስታዬን ለነገ አልቀጥርም። ባለኝ ረክቼ ዛሬ ሀሴት አደርጋለሁ።

ኤርሚያስ ኪሮስ (ካውንስሊንግ ሳይኮሎጂስት)
329 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 19:10:54 አልችልም ልረሳሽ.
-----------------------
ዉዴ እንደምን አለሽ እኔ እንዳለሁ አለሁ
በሀሳብ ስዋትት ቀኑን አልፈዋለሁ
ሌቱን ደግሞ በእንባ ሳነባ አነጋለሁ
ያው ወጉ ሆኖ እንጅ መሣቅ መጫወቴ ለይምሰል ነው እንጅ መብላት መጠጣቴ
ከተጣላሁ ቆየሁ ከራስ ማንነቴ
.
.
.
By Belaya
ሙሉውን ለማግኘት
@belayayenew
503 viewsbelaya, 16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 14:55:57 አልችልም ልረሳሽ.
-----------------------
ዉዴ እንደምን አለሽ እኔ እንዳለሁ አለሁ
በሀሳብ ስዋትት ቀኑን አልፈዋለሁ
ሌቱን ደግሞ በእንባ ሳነባ አነጋለሁ
ያው ወጉ ሆኖ እንጅ መሣቅ መጫወቴ ለይምሰል ነው እንጅ መብላት መጠጣቴ
ከተጣላሁ ቆየሁ ከራስ ማንነቴ።
754 viewsbelaya, 11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ