Get Mystery Box with random crypto!

#የእሳት_ራት በኩራዝ መካከል ከንፈሽ ስትርገበገቢ፣ ገምቼ ነበረ ከድጥ እንድትገቢ። ልትሆኚ መሄድሽ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

#የእሳት_ራት
በኩራዝ መካከል ከንፈሽ ስትርገበገቢ፣
ገምቼ ነበረ ከድጥ እንድትገቢ።
ልትሆኚ መሄድሽ የእሳት ራት፣
ደ'ሞ ምን ሊፈይድ ከነበልባል መዳራት።
ዘው ለማለቱ አትይም ይፋጃል፣
ማን ከጋመ ቧልት ይቀለምዳል።
የቀን ጎዶሎ ሲያሮጥ ያመጣሽ፣
በሻማ ውሃ ቀቅሎ ቀጣሽ።
ጓድሽም እንዲያው ናት ያንቺ ዘመድ፣
ማሰሪያ ሳታበጅ ገምጅታ ማጥመድ።
ፍቅሬ አዘንኩለት የዳሰስሁት ገላ፣
በክሩ ሰደድ ተጨምቆ ሲበላ።
#መኮን_ዮሴፍ(ባቢ)