Get Mystery Box with random crypto!

#ስም_ያለው ያኔ በፍቅራችን ድንቁ ጊዜ፣ ሳይለቀን በፊት የቁልምጫ አባዜ። ሞክሼን ስትጠሪው አቤት | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

#ስም_ያለው
ያኔ በፍቅራችን ድንቁ ጊዜ፣
ሳይለቀን በፊት የቁልምጫ አባዜ።
ሞክሼን ስትጠሪው አቤት ብዬ ነበር፣
ስም ያለው ሞኝ ነው ሲደናበር።
ሞረሽን ስትፈልጊ ወዬ እልሻለሁ፣
እኔን እየመሰለኝ ቀልቤን እገብርልሻለሁ።
ዛሬስ ልቀይረው መባሌ ካለቀረ፣
የሴጣን ጎረቤት ለመልሴ ካቃረ።
አልበጀኝምና ለወጥኩት እንግዲህ እናኔ፣
አንቺ ነሽ ምታወቂው የህይወት ምናኔ።
አውጪልኝ ባክሽ አጣሁኝ ምትክ፣
ንሰሐ አባቴ አይስሙ ለራሴ ብርክርክ።
#መኮንን_ዮሴፍ(ባቢ)