Get Mystery Box with random crypto!

ህይወታችን ላይ ትልቅ በጎ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ 10 አመለካከቶች! 1. ራሴን ለመውደድና ለመቀበል ሰ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ህይወታችን ላይ ትልቅ በጎ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ 10 አመለካከቶች!

1. ራሴን ለመውደድና ለመቀበል ሰዎች እስኪወዱኝና እስኪቀበሉኝ አልጠብቅም።

2. ትክክለኛውን ነገር አደርጋለሁ እንጂ ሰዎችን ሁሉ ለማስደሰት አልሞክርም።

3. ትችቶች እንዲያስተምሩኝ እንጂ እንዲሰብሩኝ አልፈቅድም።

4. እኔ በስህተቶቼ define አልደረገም።

5. ስህተቶቼን ከስኬቶቼ በላይ አግዝፌ አላይም።

6. ሰዎች ሁሉ እንደኔ እንዲያስቡ አልጠብቅም።

7. የማልቀይራቸውን ሀቆች እቀበላለሁ።

8. ሰዎች እንዲያማክሩኝ እንጂ እንዲወስኑልኝ አልፈቅድም።

9. በማልቀይረው ትላንት ላይ ሳይሆን ባለኝ ዛሬ ላይ አተኩራለሁ ።

10. ደስታዬን ለነገ አልቀጥርም። ባለኝ ረክቼ ዛሬ ሀሴት አደርጋለሁ።

ኤርሚያስ ኪሮስ (ካውንስሊንግ ሳይኮሎጂስት)