Get Mystery Box with random crypto!

#አንድ_ያጣላል በእዛ በማዕዱ በፍቅር ገበታ፣ አጉራሽ መርህ አለው መንታ። አንድ ያጣላል ብዬ ብደግ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

#አንድ_ያጣላል
በእዛ በማዕዱ በፍቅር ገበታ፣
አጉራሽ መርህ አለው መንታ።
አንድ ያጣላል ብዬ ብደግማት፣
ጉሮሮዋ ጠቦ የአሳ እሾህ አነቃት።
ያልሽኝ በከንቱ ሁለት ያፋቅር፣
ለምን ሆነና ቧጦ ባያቅር።
ለፆመኛ ዳገት ደሙን አቀዝቅዞ፣
ልውረድ ልውረድ ይላል እንጥል አመርቅዞ።
አይ እማ ብትገላግያት ተቆርጦ፣
አፎይ ማለት እንጂ ቁስል ተፍረጥርጦ።
አትፍሪ ክስ ካለፈውስ አካሚ፣
በሽታውን ያውቃል የተጋጨውን ታማሚ።
መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)