Get Mystery Box with random crypto!

#ጽጌሬዳ_ለብሰሽ አበባይቱ ፍቅሬ ከቀጠሮው ቦታ፣ ጽጌሬዳ ለብሰሽ ነይ የመውደድን ኩታ። ከቀለም መ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

#ጽጌሬዳ_ለብሰሽ
አበባይቱ ፍቅሬ ከቀጠሮው ቦታ፣
ጽጌሬዳ ለብሰሽ ነይ የመውደድን ኩታ።
ከቀለም መርጠሽ የደመቀ ቀይ፣
በይፋ አወጀሽ የሱ ነኝ በይ።
እኔም ጠብቅሻለሁ በቢራቢሮ ከረቫት፣
አንገቴን አስሬ ልቤንም ስፈታት።
ከመክተሚያችን ብታዪ ቄስ የጠመጠመ፣
አትስጊ ግቢ ነው ሊያስተሳስረን የተሾመ።
#መኮንን_ዮሴፍ(ባቢ)