Get Mystery Box with random crypto!

ቅቤ ቀቢዎቹ ቅቤ ይመስል ደም እየቀቡሽ፣ ከፊትሽ ወዘና ቀድተው አገረጡሽ። ሙት ተጥሎበት ቀዬሽ በከ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ቅቤ ቀቢዎቹ
ቅቤ ይመስል ደም እየቀቡሽ፣
ከፊትሽ ወዘና ቀድተው አገረጡሽ።
ሙት ተጥሎበት ቀዬሽ በከተ፣
ማስረሻ ልጅሽም ስንዝር አልመከተ።
በል አስረሴ አርዳት ሌሊትም አይደለ፣
የአብራኳ ክፋይ ቁልቁል እንደተገደለ።
ያን ግንበኛ ቤቱን ቀይ የለቀለቀ፣
በመዝገብ በችሎት እንዲያስጠይቀው ያላወቀ።
ሸሚዙ ቀለም ነክቶት ቢያዩ፣
አሻራ ፍለጋ ሳምንት ተወያዩ፣
ከገዳይ ጋር ባርኔጣ ነስተው ተለያዩ።
ሀገሬ ድንጋይሽ መንገድ ዘጋ፣
ትውልድሽ በሙሉ ሆ ብሎ አዛጋ።