Get Mystery Box with random crypto!

#ኖር ተቀበይ እንግዳሽ ነኝ በኖር፣ ከልብሽ ጠልቄ በተድላ እንድኖር። ከኩራትሽ ወንበር ትንሽ ተነሺ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

#ኖር
ተቀበይ እንግዳሽ ነኝ በኖር፣
ከልብሽ ጠልቄ በተድላ እንድኖር።
ከኩራትሽ ወንበር ትንሽ ተነሺ፣
የምታድሪው አይደለም ጤና ስትነሺ።
እኔም እመልሳለሁ በእግዜር ሰላምታ፣
እንድትሰነብት መንፈሴ ከነፍስሽ ተስማምታ።
ብቻ እንዳይቆየኝ በርሽ ተጠርቅሞ፣
ደጅ መጥናት አልፈልግም ቆሞ።
ለምን ሳይወልቅ የአያትሽ ባርኔጣ፣
እንዴት ሳይታጠፍ የሚያነቡት ጋዜጣ፣
የወደፊት ባልሽ ከቤታቸው ስመጣ።
ባይተዋርነት ተሰማኝ ፀጉረ ልውጥነት፣
የሰው ልጅ ባህሪ ሲስት ወጥነት።
#መኮንን_ዮሴፍ(ባቢ)