Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የሰርጥ አድራሻ: @gitmnamuzika
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.30K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብበት ቻናል ነው ይከታተሉ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ ሚክስ ከፌሊኖቫ ጋር
Creator@fellynovaa
Invite link to share
https://t.me/ vKDN0lXKiKFmN2M0

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-02-03 00:55:39 #አህያ_ከአመዱ
በዚህች ብሄርተኛ የአያት ሀገር፣
ዘመድ ከዘመዱ ተብሎ ሲነገር።
ጎሳህን አስቀድም ነው ትርጉሙ፣
የወንዝ ልጅ ስለሆነ ደሙ።
ደግሞ እኮ በአህያ ያድበሰብዋል፣
ፍም አመዱን ለክምር ያግበሰብሰዋል።
ጠብደሉ እንስሳ ጀርባው በማበዱ፣
መታከክን ቢመረጥ ለእፎይታ መንገዱ።
ተረፈ ለሰው ዘር ትስስር፣
ግንድነትን ትቶ መጣላት በስር።
ቢገባው ከስጋው የቅርብ ጎረቤቱ፣
ራስ ነበር አፍ አንደበቱ።
    የብዕር ስም:#ማክቤል
         plz share
1.4K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 21:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 10:03:42 የግጥም መናሐሪያ :
ቀያይ ሰማያት
ምዕራባዊ አጽናፍ ቀይ ሰማይ ታየኝ፣
መሬት ከዛቢያዋ ልጠልቅ መሰለኝ።
ሰማይ ቢታጠፍም እስከ ሰባተኛ፣
አይንሽን ሳላየው አልችልም ልተኛ።
መንበሩ ቢሰፋ ቆሞ ከመንግስቱ፣
አያግደኝም ጊዜ ነው ምሽቱ።
ጽድቅና ኩነኔ ቢሆን የሱ ምንጣፍ፣
ለምነው ሚላላ አፈቅርሻለሁ ሲፃፍ።
ከጠፈር ጠረፍ ላይ ከሕዋው መጥቆ፣
የሞትኩልሽ ፈሊጥ ቢለፈፍ ለጥቆ።
በአሸን ክዋክብት ይታጀባል እንጂ፣
ደም አይለቀስም ለጨረቃ ፍጂ።
                መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)

#ሳትደግስ_አትጣላም
አንተ አምላኬ የህይወቴ ቁልፍ፣
እልፍ አሳየኸኝ ስል እልፍ።
ለካ በርህን አልዘጋግህም መስኮቱን ሳትከፍት፣
እኔማ ብዬ ነበር የዕድሌ ልክፍት።
አዎ ገባኝ አሁን ሳትደግስ አትጣላም፣
እቅፍ ካንተ ውጪ አይደላም።
   መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)
724 viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 17:25:57 ሁለቱም ዓይኖቼ
እምባ ያፈሳሉ
ካላንቺ ሌላ ሴት
አናይም ይላሉ
1.5K views༺ Gutu.Z ༻, 14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 11:04:24 ልንገራት?ንገራት!!

የኔ ፍቅር ላላጣት እራሴን ጎዳሁ ሳልነግራት
ወይ ነግሬአት አላረፍኩ ፍቅሬን አልተነፈስኩ
እንዲሁ ጭንቀት እራሴን እየወቀስሁ

ነግሬአት እህትነትዋ ከማጣ ከምትርቅ ካጠገቤ
ወይ ደግሞ እሺ ብላኝ ገደብ የለሽ ደስታ ላዘነላት ልቤ

አውይ አሁንማ ሲቃዬ በዛ ልጥራት ካለችበት
እሷን ሳይሆን ሌላ እንዳፈቀርኩ ላማክራት እንዳልኩ

አንተኮ ጥሩ ሰው ብላ እንደጀመረች አለችኝ ንገራት
እኔም እሺ ብዬ እሷ መሆናን ስነግራት እኔን ለመውገር ድንጋይ ነው የቀራት

  ወይ ልንገራት?ንገራት!
   Sam to Mar
1.5K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, edited  08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 11:03:22 አምስት ጠቃሚ ምክሮች!

❶ ስኬት ጉዞ ነው:- ስኬት የማያቋርጥ የእድሜልክ የህይወት ጉዞ እንጂ መዳረሻ አይደለም።

❷ ያለፈው አልፏል:- ትላንት ማለፉን በመገንዘብ፣ በትላንት ስህተት እና ድክመቶች ከመቆጨት ለነገ ትምህርት መውሰድ።

❸ ዛሬ አዲስ ቀን ነው:- ትላንት አልፏል በዛሬ ግን ነገን ማስተካከል ይቻላል።

❹ ማንም ፍፁም አይደለም:- ፈተና ወይም ተግዳሮት የህይወት አንዱ አካል በመሆኑ በህይወት ጉዞ ወሰጥ መውደቅ እና መነሳት እንደሚያጋጥም በመረዳት ዝግጁ መሆን።

❺ ለበጎ ነው:- እያንዳንዱ መጥፎም ሆነ ጥሩ ክስተት ለነገ የተሻለ ውጤት እና ስኬት አስተማሪ መሆኑን መገንዘብ።

መለካም ቀን
1.4K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, edited  08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 22:27:38 \\እንደሾመሽ ልቤ ሻረሽ//

ልቤ አመኖሽ ነበር
ታማኝ ነሽ ብሎ
ማቼም ላይለይሽ
ቃል ገብቶልሽ ምሎ
ግን ምን ያደርጋል
ያሁሉ መሃላ
ቃልሽን ልትረሽዉ
እንድህ በስተኋላ
እኔ አንቴን ካጣዉ
አልኖርም ሞታለዉ
ወይ መርዝ ጠጥቼ
ራሴን አጠፋለዉ
ስትይኝ ነበሬ
ያኔ ሳንለያይ
ዛሬስ ርቀሺኛል
አይንሽን እንዳላይ

እራሴን ሰጥቸሽ
ባመንኩሽ ከልቤ
ወዳጅ ዘመድ ሳልል
ባፈቅርሽ ቀርቤ
ሁሉም ተረሳና
ክደት ሆኔ መልሴ
ይሁን እስቲ ይሁን
ልኑር ብቻዬኒ
እስቲ ምን እንደሚል
ልስማዉ ገታዬኒ
ሃዘኔ ብበዛም
ባይተዋር ሆኜ
የኔ የምለዉ ባጣ
ሰዉ ጠፍቶ ከጎኔ
ባምላኬ አምናለዉ
በሱ ተስፋ ኣልቆርጥም
አንገቴን ሰብሬ
ስተክዝ ኣልኖርመ

አይይይ….

በጣም ይገርመኛል
ሳስበዉ አንዳንዴ
ፈጣሪም እንደ ሰዉ
ጠልቶኝ ይሆን እንዴ
ብዬ አስባለዉ
ስሰማኝ ሃዘኔ
ሞት እና ተስፋ መቁረጥ
ስመጣ ወደኔ
እስቲ ልጠይቅሽ
ንገሪኝ እዉነቱን
ማነዉ ያስተማረሽ
ጨክኖ መክዳቱን??
ዓይኔና ልቤ
ሕዎቴ እያለሽ
እርግፍ አርጎ መርሳት
ማነዉ ያስተማረሽ?
እስቲ መልስ ስጪኝ
ልወቀዉ እዉነቱን
እይንህን ለአፈር
ብለሽ የማለቱን

አለሜ

ልብሽ እያወቄ
ችዬ እንደማልተዉሽ
እንዴት እንደቀላል
ቶሎ ተረሳሁሽ??
ያኔ ብዬሽ ነበር
የኔ ፋና ወጊ
የልቤን የሆዴን
ሁሉን የምታዉቂ
ዛሬ ብቻዬን ነኝ
ባዶ ነዉ ሕይወቴ
ቅስሜም ተሰብሯል
መክኗል ምኞቴ
ስንቴስ አስከፋሺኝ
ስንቴስ አሳዘንሺኝ
የዋህዉን ልቤን
ነክተሸ አደማሺኝ

አዎ ውዴ

ወድጄሽ ነበሬ
በእዉነተኛዉ ፍቅር
እንዲህ ከምሆንማ
ይቅር በቃ ይቅር
ልቤ ንግስት አርጎ
እራሱ እንደሾመሽ
ዛሬ ስታደሚዉ
ተስፋ ቆርጦ ሻረሽ

1.6K views༺ Gutu.Z ༻, 19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 20:32:36 ገና በልጅነት ስመከር በታላቅ
ተብዬ ነበረ ሚስጥርህን ጠብቅ
ሚስጥር ለመጠበቅ ቃል ገብቻለሁ
ቃል ከባድ መሆኑን ዛሬ አውቄአለሁ
ሚስጥር መጠበቅ አደራ ሆኖብኝ
አንቺን ማፍቀሬን ከራስሽ ደበኩኝ
ዛሬ ግን ጨክኜ አደራዬን ላወርድ
ወዳንቺ ስመጣ በፍቅር መንገድ
ፊደል ለቃቅሜ ቃላቶች መስርቼ
ልክ እንደጀግና ልነግርሽ መጥቼ
ጓደኞችሽ መጡ ዙሪያዬን ከበቡኝ
ፍቅረኛ አላት ብለው ወደኋላ ገፉኝ
መልከመልካም ቆንጆ ፀባይን ጨምሮ
በጣም ተቸገረ ልቤ አንቺን አፍቅሮ
አንድ አመት ካለፈኝ ሆነኝ ሁለት ወር
ልቤ በመናፈቅ አንቺን በማፍቀር
ይኸው እወቂልኝ በጋራ እናድርገው
እኔ ለብቻዬ እንዴት ልሸከመው
ፍቅር ቀልድ አደለም አይወራም በሜዳ
አይተሽ ተረጂልኝ የሚስጥሬን ጓዳ
ተመስገን ፈጣሪ የውስጤን አወቀች
ሚስጥሬን ተረድታ እሺ ይሁን አለች
ቀና አልኩኝና ሳልጨርስ ምስጋና
ከሌላኛው ጋር ሄደች እንደገና
አንቺ ግን ጀግና ነሽ ደግሜ ላስታውስሽ
ልቤን የማረክሺው የመጀመሪያዬ ነሽ
ስለዚህ ፍቅሬ ሆይ ስሚኝ ልንገርሽ
የኔ ባትሆኚም እንኳን እንደምወድሽ
.
.
.
.
.
1.5K viewsŦıņ§ĥų ¥ěĥűªľą§ĥ€ŧ, 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 09:59:27 እኔ እና ሚስቴ(ከ "ሀ" እስከ"ፐ")
====================
ከእለታት በአንድ ቀን...(ከ "ሀ" -"ሃ")
እረፍት ስለፈለኩ
ከአልጋየ ተጋደምኩ
ግና ምን ያደርጋል
ቀኝ አይኔን ሸከከኝ
ግራ ጎኔን ወጋኝ
ከአልጋየ ወርጄ ከቤቴ ወጣሁኝ
መንገድ ዳር
ቁጭ ብየ በሀሳብ ነጎድኩኝ

የወጋኝን ጎኔን በእጄ ስዳብሰው
ጎሏል አንድ ነገር ጎሎኛል አንድ ሰው
ፈለኩኝ ሄዋኔን
ከሞላው ህዝብ ላይ ከሚተራመሰው
የሸከከኝ አይኔን ወረወርኩት እሩቅ
የወጋኝን ጎኔን
መድሀኒት እስኪአገኝ ደባበስኩት በጥብቅ
አፌንም ነገርኩት
ሄዋኔን ለመሳብ ብዙ ቃላት ሰንቅ
ጥርሴንም መከርኩት
ሄዋኔን ለማስመጥ ልመድ ብዙ መሳቅ
ይኧው ...ከምክሩ በሗላ ሁሉን አሟልቸ
አይኔ እስኪአመጣልኝ አለሁ ተጎልቼ!!
by belaya

እስከ "ፐ" ያለው ታሪክ ይቀጥል የምትሉ በ" " ግለፁ።ያላችሁን ሀሳብ ደግሞ comment ላይ አስቀምጡልኝ
1.7K viewsbelaya, edited  06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 22:19:28 ቀያይ ሰማያት
ምዕራባዊ አጽናፍ ቀይ ሰማይ ታየኝ፣
መሬት ከዛቢያዋ ልጠልቅ መሰለኝ።
ሰማይ ቢታጠፍም እስከ ሰባተኛ፣
አይንሽን ሳላየው አልችልም ልተኛ።
መንበሩ ቢሰፋ ቆሞ ከመንግስቱ፣
አያግደኝም ጊዜ ነው ምሽቱ።
ጽድቅና ኩነኔ ቢሆን የሱ ምንጣፍ፣
ለምነው ሚላላ አፈቅርሻለሁ ሲፃፍ።
ከጠፈር ጠረፍ ላይ ከሕዋው መጥቆ፣
የሞትኩልሽ ፈሊጥ ቢለፈፍ ለጥቆ።
በአሸን ክዋክብት ይታጀባል እንጂ፣
ደም አይለቀስም ለጨረቃ ፍጂ።
                መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)
1.8K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 22:15:57 የሚሰሩትን ይበልጥ እንዲወዱት የሚያግዙ አምስት ጠቃሚ ነጥቦች፦

- በእቅድ መመራት
- ለፈተናዎች እራስን ማዘጋጀት
- አስደሳች የስራን አካባቢ መፍጠር
- እረፍትን በአግባቡ መጠቀም
- ስራን ወደቤት አለመውሰድ

መልካም የስራ ሳምንት!የሚሰሩትን ይበልጥ እንዲወዱት የሚያግዙ አምስት ጠቃሚ ነጥቦች፦

- በእቅድ መመራት
- ለፈተናዎች እራስን ማዘጋጀት
- አስደሳች የስራን አካባቢ መፍጠር
- እረፍትን በአግባቡ መጠቀም
- ስራን ወደቤት አለመውሰድ

መልካም የስራ ሳምንት!

 
1.8K viewsFellyNova/ፌሊኖቫ, 19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ