Get Mystery Box with random crypto!

#አህያ_ከአመዱ በዚህች ብሄርተኛ የአያት ሀገር፣ ዘመድ ከዘመዱ ተብሎ ሲነገር። ጎሳህን አስቀድም ነ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

#አህያ_ከአመዱ
በዚህች ብሄርተኛ የአያት ሀገር፣
ዘመድ ከዘመዱ ተብሎ ሲነገር።
ጎሳህን አስቀድም ነው ትርጉሙ፣
የወንዝ ልጅ ስለሆነ ደሙ።
ደግሞ እኮ በአህያ ያድበሰብዋል፣
ፍም አመዱን ለክምር ያግበሰብሰዋል።
ጠብደሉ እንስሳ ጀርባው በማበዱ፣
መታከክን ቢመረጥ ለእፎይታ መንገዱ።
ተረፈ ለሰው ዘር ትስስር፣
ግንድነትን ትቶ መጣላት በስር።
ቢገባው ከስጋው የቅርብ ጎረቤቱ፣
ራስ ነበር አፍ አንደበቱ።
    የብዕር ስም:#ማክቤል
         plz share