Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የሰርጥ አድራሻ: @gitmnamuzika
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.30K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብበት ቻናል ነው ይከታተሉ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ ሚክስ ከፌሊኖቫ ጋር
Creator@fellynovaa
Invite link to share
https://t.me/ vKDN0lXKiKFmN2M0

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-02 12:49:08 (በላይ በቀለ ወያ)
.
.
አንቺ ሚያስጨንቅሽ
የአንዲት ቆንጅዬ አርቲስት ፣ የአለባበስ ፋሽን
እኔን ሚያስጨንቀኝ
እንዴት እንደማወልቅ ፣ በፆም ቀሚስሽን
።።።
አንቺን ሚያስገርምሽ ፣ ሴት ስትታይ እርቃን
እኔን ሚያስገርመኝ
ከየት እንደተገኘ ፣ ይሔ ሁሉ ፃድቃን
።።
አንቺን ሚያሳስብሽ
የሰው አለባበስ ፣ የሰው አካሔዱ
እኔ ሚያሳስበኝ
ጤፍ በርበሬ ሽሮ ፣ ዘይት መወደዱ
የሰው ልጅ እንደበግ ፣ ሰርክ መታረዱ።
።።።
በምን እንግባባ ፣ ታዲያ እኔና አንቺ
አንቺ ሚያስጨንቅሽ ፣ የሰው ትዳር ፍቺ
እኔን ሚያስጨንቀኝ
በየ መታጠፊያ ፣ ያለ ማጅራት መቺ
ወሬያችን አንድነት ፣ ኑሯችን ለየቅል
አንቺ ሚያምርሽ ልቤ ፣ እኔ ሚያምረኝ ቅቅል (የድንች )
የኔ ተስፋ አንድነት ፣ያንቺ ተስፋ አንድ ቀን
ቋንቋ እንዴት ያግባባን ፣ ኑሮ እያራራቀን?
712 viewsbelaya, 09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 21:02:41 "ዝም በል"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
ከሳሽህ ፊት ዘንበል
ሰዳቢህ ፊት ዘንበል
በነፍስህ ተናገር በቃልህ ዝም በል።

ዝም

እሺ በል አጎንብስ
ፊደል አታገግበስብስ
ዝም በል ጭጭ ጭጭ
ስንፍናን በልምጭ
ዝምታህን እቅጭ
አድርገህ ተቀበል
ዝም ብለህ አስጩህ እንደቅዱስ ፀበል::

አስብ ዝም ብለህ
እንደሊቅ ተራቀቅ
እንደንጉሥ ውደቅ::

ዝም ብለህ ሞክር
ዝም ብለህ ጨክን
ዝምበል ተንገዳገድ
ማስራዳት ሲያስብ ነው ሰው የሚወላገድ::

ዝም::

እግዜርን ተመልከት
ሊያስረዳህ ሲሞክር አታየውም ሲጥር
መች ብዙ አወራ ዓለምን ሲፈጥር።

(ዝም ብለህ ቀጥል
203 viewsbelaya, 18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 10:45:02
እኔ እና አልጋዬ

ጠዋት ወገግ ብላ ፀሀይ ስትኩነሰነስ፣
ከአልጋዬ አሻግራ የዛሬ ፀዳሏን ሜሮኗን ስታፈስ፣

ልቤ ተስፍ ታይቶት መብት በሌለበት ነፍሱ፣
በአምላክ ቸርነት ከፀሀይ ተቀባ ሰው ሊሆን ለእርሱ፣

እኔ
በአልጋዬ ማዶ፥ ሰመመን የወጋኚ፣
ትራስ ብርድ ልብሱን አፅንቼ ማልጠብቅ፥ የደካሞች መናኚ፣

በመገላበጥ አለት ስናጥ ማድር ሌቴን፣
ግብዝ አልባልም ወይ ?
ባላመሰግን ስነቃ አምላኬን፣

_ __

ግዕዝ ሙላት

@geez_mulat
683 viewsጥ ቁር ዝምታ, 07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 10:00:34 ክፍል ምናምን

ዮሮና ከዕንቅልፉ ሲነቃ፤ ነጭናጫ ሚስቱን አጠገቡ ቆማ አገኛት። ዓይኖቹን ለመግለጥ እየታገለ፤ ለመነሳት ሲሞክር ሀያሉ ዕንቅልፍ በኩርኩም ብሎ አጋደመው።

ሚስት በንዴት አንሶላውን ከ ላዩ ላይ ገፈፈች፤ ድንብርብር እያለ ከዕንቅልፉ ተነሳ።

"በራችን ላይ ሌባ ተኝቷል ፤ አንተ እዚ ተጋድመህልኛል። ጋድሚያም።" ወገቧን ይዛ እየተውረገረገች ነበር የተናገረችው።

" ሌባ በዚህ ሰዓት ምን ያስተኛዋል፤ ወደ ስራው ይሰማራል እንጂ። " አለ በሩን ከፍቶ ቢወጣ የውጭውን ቅዝቃዜ ሲያስበው እየዘገነነው።

"እና እኛ በር ላይ ነው የሚተኛው?? በራችን ሲደፈር ዝም እንበል??" ሚስት በገነች።

* ****

" በራችን ሲደፈር ዝም እንበል??" አሁን አንድ ነገር ቢፈጠር የምታግዝ አትመስልም?? ወይኔ ዮሮና የማንም አሮጊት መጫወቻ ልሁን??

"ሴትዮ በዚህ ብርድ አልወጣም" እንደ አባወራነቴ ቆጣ ብዬ።

"ሊቆጡም ያምሮዎታል?? ድሮስ የርስዎ አምባገነንነት በኛ ላይ ነው እንጂ ።"

ኡፍ አሽሙሯን ጀመረችኝ። ቀጥታ ቢናገሩ ጥፊ እንቀምሳለንን የፈሩ ሚስቶች ማጥቂያ፤ አሽሙር።

የሚፈልጉት ነገር ካልተደረ፤ ቀኑን ማጉረምረም፤ማማረር መነጫነጭ።

ንጭንጭን እንደ ጦር መሣሪያ መጠቀም፤

ሁፍ ምነው ባለትዳር ባልሆንኩ፤ መች ቀን ነው ያገባሁት ብሎ ማማረር፤ ሲያገቡ እንዳልተደሰቱ፤ የፍቅር ጥያቄያቸው ምላሽ ሲያገኝ እንዳልፈነጠዙ።


*
ቀና ሲል ዕንቅልፍ ወስዶት እንደነበር ተረዳ፤ የላይብረሪ ተቆጣጣሪው ነበር ከ ዕንቅልፉ የቀሰቀሰው።
597 viewsያቢ ነኝ, 07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 22:10:34 ዮሮና ቤተ መጻሕፍት ገብቶ ለነገው ፈተና እያነበበ ነበር።

ድንገት ስልኩ ኖቲፊኬሽን አመጣለት። በቴሌቪዥን የሚታይ አስቂኝ ሲትኮም ነበር፤ በአንድ ደስተኛ ቤተሰብ ዙርያ የሚያጠነጥን ነበር ታሪኩ።

ሚስት ባልን ከተኛበት ትቀሰቅሰዋለች፤ ባል ከ ዕንቅልፉ እየተነጫነጨ ተነሳ፤

ሚስት፡ በረንዳው ላይ የተኛ ሰው አለ

ባል፡ ማን አባቱ ነው? ( እንደፈራ ሁኔታው ይናገራል፤ እንዳልፈራም ለማስመሰል ይጥራል።)

ሚስት፡ ፈራህ እንዴ??

ባል፡ ምን ያስፈራኛል?( ቆጣ ብሎ)

በሩ ላይ ባል እየተንጎራደደ ይሁን እየተወላገደ ባለየለት ፤ ቅጥ ያጣ እንቅስቃሴ ያካሂዳል።

ዮሮና ሲትኮሙ እስኪያልቅ በፈገግታ ነበር ሲከታተል የቆየው ።

ቤተሰብ ቢኖረኝ ሲል ተመኘ፤ ቤተሰብ ቢኖረው እንዴት ደስተኛ ሊሆን እንደሚችል አሰበ።
287 viewsያቢ ነኝ, 19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 19:25:43 ሁልጊዜ በሕልሙ ወደ አንድ መንደር ይጓዝ ነበር። በብርቱካን የተከበበች መንደር፤ በመንደሯ ከብርቱካን በስተቀር የሚታይ የአትክልት ዘር የለም፤ ተጠጋግተው የተሰሩ ቤቶች፤ የብርቱካን ተክሎች።

ይሔንን መንደር ድጋግሞ በሕልሙ በማየቱ የተነሳ የሚያውቀው የሚያውቀው ይመስለዋል።

"ዮሮና ተነስ ቁርስ ደርሷል" መንትያ እህቱ ነበረች የቀሰቀሰችው።
520 viewsያቢ ነኝ, 16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 19:24:34 የዶርም ጓደኞቹ በሙሉ ወደ ክፍል ሄደዋል።

ታሞ ክላስ መቅጣት ከጀመረ ሳምንት ሊሆነው ነው።

ወደ ሞት የተቃረበ ይመስለዋል፤ የልጅነት ትውስታዎቹ ያላንዳች መደብዘዝ ቅርብጭ ብለው ይታዩት ጀምሯል።

ከልጅነት ጓደኞቹ ጋር ውሀ ላይ ለ ሶስት ሆነው ሲሸኑ፤ ገጠር እያሉ አጎዛ አንጥፈው ሲተኙ፤ በሌሊት የጅብ ጩኽት፤ አልጋ ላይ ሸንቶ አያቱ የቆነጠጡት።

ትውስታዎቹ ምስል ፈጥረው ፤ አጠገቡ ሆነው ታዩት።

በየቀኑ ሕመሙ እየባሰበት ሲሄድ ይሰማዋል።
483 viewsያቢ ነኝ, 16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 15:25:51 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲገባ፤ ብዙ ጓደኞች አፈራ። በተለይ ማህራበረሰቡ ከሚንቃቸው መና ከሚባሉ ዘሮች ጋር ተግባባ። መናዎች የዛር የልጅ ልጅ ናቸው ተብሎ ይታመን ነበር።በሰው አዕምሮ ውስጥ መግባት እንደሚችሉ ይታመናል። ከዛር የሚለዩት እንደሰው ስጋ ለባሽ በመሆናቸው ነው ። ዛሮች በሌላ ሰው አካል ውስጥ ካልኖሩ በስተቀር ሕይወት የላቸውም ጥገኛ ፓራሳይት ናቸው።

የዮሮና ጓደኞች በብዛት ከ መና ማህበረሰብ ስለነበር ፤ ብዙን ግዜ ቤተሰቡን የሚያውቁ ጓደኞቹ ይመክሩትና ያስጠነቅቁት ነበር


































657 views12:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 15:24:48 የነ ዮሮና ሰራተኛ ታማ ፀበል ገባች። በሰፈሩ ስለሷ ብዙ ተወራ፤ ሌሊት በዕንቅልፍ ልቧ የመጓዝ ልማድ ነበረባት አሉ። አንዳንዶች ደግሞ በዘር የሚዋረስ ዛር አለባት አሉ። ሌሎችም በቀትር ወንዝ ስትሄድ ጋኔል ለክፏት ነው አሉ።


ዕንጨት ሰበራ ስትሄድ ፤ ጫካ ውስጥ ቡና የሚጠጡ ሰይጣኖችን ደርሳባቸው ነው በሽተኛ ያረጓት።

ብዙ ብዙ ተባለ፤ ቡዳ በልቷት ነው ያሉም አሉ።

ዮሮና ግን ምሽት አብረው ያሳለፉት፤ ትዝታው ብቻ በአዕምሮው ቀረ። ደጋግሞ ስለነዛ ምሽቶች ያልማል።
522 views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ