Get Mystery Box with random crypto!

'ዝም በል' ኤልያስ ሽታኹን ~ ~ ~ ~ ~ ከሳሽህ ፊት | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

"ዝም በል"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
ከሳሽህ ፊት ዘንበል
ሰዳቢህ ፊት ዘንበል
በነፍስህ ተናገር በቃልህ ዝም በል።

ዝም

እሺ በል አጎንብስ
ፊደል አታገግበስብስ
ዝም በል ጭጭ ጭጭ
ስንፍናን በልምጭ
ዝምታህን እቅጭ
አድርገህ ተቀበል
ዝም ብለህ አስጩህ እንደቅዱስ ፀበል::

አስብ ዝም ብለህ
እንደሊቅ ተራቀቅ
እንደንጉሥ ውደቅ::

ዝም ብለህ ሞክር
ዝም ብለህ ጨክን
ዝምበል ተንገዳገድ
ማስራዳት ሲያስብ ነው ሰው የሚወላገድ::

ዝም::

እግዜርን ተመልከት
ሊያስረዳህ ሲሞክር አታየውም ሲጥር
መች ብዙ አወራ ዓለምን ሲፈጥር።

(ዝም ብለህ ቀጥል