Get Mystery Box with random crypto!

(በላይ በቀለ ወያ) . . አንቺ ሚያስጨንቅሽ የአንዲት ቆንጅዬ አርቲስት ፣ የአለባበስ ፋሽን እኔን | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
አንቺ ሚያስጨንቅሽ
የአንዲት ቆንጅዬ አርቲስት ፣ የአለባበስ ፋሽን
እኔን ሚያስጨንቀኝ
እንዴት እንደማወልቅ ፣ በፆም ቀሚስሽን
።።።
አንቺን ሚያስገርምሽ ፣ ሴት ስትታይ እርቃን
እኔን ሚያስገርመኝ
ከየት እንደተገኘ ፣ ይሔ ሁሉ ፃድቃን
።።
አንቺን ሚያሳስብሽ
የሰው አለባበስ ፣ የሰው አካሔዱ
እኔ ሚያሳስበኝ
ጤፍ በርበሬ ሽሮ ፣ ዘይት መወደዱ
የሰው ልጅ እንደበግ ፣ ሰርክ መታረዱ።
።።።
በምን እንግባባ ፣ ታዲያ እኔና አንቺ
አንቺ ሚያስጨንቅሽ ፣ የሰው ትዳር ፍቺ
እኔን ሚያስጨንቀኝ
በየ መታጠፊያ ፣ ያለ ማጅራት መቺ
ወሬያችን አንድነት ፣ ኑሯችን ለየቅል
አንቺ ሚያምርሽ ልቤ ፣ እኔ ሚያምረኝ ቅቅል (የድንች )
የኔ ተስፋ አንድነት ፣ያንቺ ተስፋ አንድ ቀን
ቋንቋ እንዴት ያግባባን ፣ ኑሮ እያራራቀን?