Get Mystery Box with random crypto!

ተናገር ብዕሬ ማስክህን አውልቀው ተናገር ብዕሬ፣ ለምን ዝም ትላለህ ስገደል በዘሬ፣ ሌባ በወጣበት | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ተናገር ብዕሬ

ማስክህን አውልቀው ተናገር ብዕሬ፣
ለምን ዝም ትላለህ ስገደል በዘሬ፣
ሌባ በወጣበት ምላስ ሻጪ ገብቶ፣
ህዝብ ሲያስጨበጭብ ምላሱን አብልቶ፣
የወጣውን ሌባ ሲነቅፍ ሲያረክስ፣
ለምስኪኑ ህዝብ ሞት ፅዋ ሲደግስ፣
እውነት ጎህ ቀደደ እውነትን ገለጠ፣
ጭብጨባው ረገበ እሮሮው በለጠ፣
አንድ ሳምንት እለቅሶ አንድ ሳምንት ዳንኪራ፣
አገር ዘማ ስታይ የራሷን መከራ፣
ምስኪን ሲፈናቀል ገዳይ ቤት ሲሰራ፣
ጭቀት ሲደራረብ በተራ በተራ፣
ብለን ስንጠይቅ አድነን ሙሴያችችን፣
ችግኝ ተከለልን ጥላ ለሬሳችን፣
ኮፈንህን አውልቀው ተናገር ብዕሬ፣
ለምን ዝም ትላለህ ስታረድ በዘሬ!
ሙሴ መጣ ብሎ ያጨበጨበን ህዝብ፣
አንገቱን ለካራ አስከሬኑን ለዝንብ
ማስክህን አውልቀው ተናገር ብዕሬ፣
ለምን ዝም ትላለህ ስሰደድ በሀገሬ።


Mak