Get Mystery Box with random crypto!

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለ፤ ከመናዎች ቀጥሎ ጎረሞቴ ከሚባሉ ዘሮች ጋር ጓደኛ ሆነ። ማታ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለ፤ ከመናዎች ቀጥሎ ጎረሞቴ ከሚባሉ ዘሮች ጋር ጓደኛ ሆነ። ማታ ማታ ጎረሞቴዎች ወደ ጅብ ይቀየራሉ የሚል አሉባልታ ነበር፤ አፈታሪኮችም በስፋት ይነገሩ ነበር።

አንድ ቀን ዮሮና፤ ስለ አፈታሪኮቹ ዕውነታነት ከ ጎረሞቴ ጓደኞቹ አንደኛውን ሊጠይቀው ወሰነ።

ልጠይቀው፤ ወይንስ በጥያቄዬ ይናደድ ይሆን?? እያለ ከራሱ ጋር ሲሟገት ከቆዬ በሗላ እንደምንም ጥያቄውን አቀረበ።

"ቡዳ ነህ??" አለ በፍርሃት የጥያቄው ምን ሊያስከትል እንደሚችል ባለማወቅ።

*









*



*



*





*






"ይላሉ።" አለው ጥያቄው ምንም ስሜት እንዳላሳደረበት ሁሉ።

" ማለት?? አይደለሁም ለማለት ነው??" አለ ዮሮና ግራ ተጋብቶ፤ ሁሉም ነገር ተረት ተረት አፈታሪክ ኖሯላ??

" የሰው ልጅ የተለየ ተሰጥዖ ይዞ ሊወለድ ይችላል። ያንን ተሰጥዖ በልምምድ ሊያሳድገው ይችላል፤ አንዳንድ ዕፅዋቶችም ሀይልህን ለማውጣት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ጀነቲክስ ወይንም ዝርያም የራሱ አስተዋፅዖ አለው። "

" እና ሰው ወደ ጅብነት ወይንም ወደ መቀየር ይችላል?"

ዮሮና በድንጋጤ ፈዞ ጠየቀ።

"ዛሬ ማታ ወደ እኔ ቤት ከመጣህ ሁሉንም በቅርቡ የምታውቀው ይሆናል።"