Get Mystery Box with random crypto!

'ጎሮሞቴ ለመሆን ወስነህ ስለመጣህና ልትቀላቀለን ስለወሰንክ ደስተኛ ነኝ።' አለ ጎሮሞቴው። 'ምን | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

"ጎሮሞቴ ለመሆን ወስነህ ስለመጣህና ልትቀላቀለን ስለወሰንክ ደስተኛ ነኝ።" አለ ጎሮሞቴው።

"ምን??" ወጥመድ ውስጥ እንደገባች ዓይጥ ሽምቅቅ አለ።

"ምነው ጎረሞቴ መሆን አትፈልግም?? አንድ የኛ ዘር የሰው ዘርን ሲያገባ ሚስቱን ወደ ጎረሞቴነት የሚለውጥበት መድሓኒት አለው። " አለ ጎረሞቴው።

"ግን ማነው ጎረሞቴ መሆን የሚፈልግ?? ማንም ጎረሞቴን ማግባት አይፈልግም።" አለ ዮቶር በመገረም።

"ምክንያቱም ስለምትንቁን??" አለ ጎረሞቴው በመኮሳተር። ዮሮና የሚናገረው ጠፍቶት ዝም ጭጭ አለ።

"ምርጫው ያንተ ነው፤ እንደ ሰዎች በባዶ ኩራትና ዝና መኮፈስ አልያም ሆነህ የዩኒቨርስን ሀይል ማጣጣም፤ የሰዎችን አዕምሮ ማንበብ ፤ በሰዎች አዕምሮ ሰርጎ መግባት፤ ጅቦችን መጋለብ...ወዘተ ወዘተ"

አለ ጎረሞቴው ለመረጋጋት እየሞከረ።

"እና ሰዎችን ማሳመም ፤ ማሰቃየት ብሎም መግደል?? መጨረሻችሁ ሲዖል ነው የሚሆነው።" ዮሮና አለች ለመከራከር በሞከረ ቁጥር ራሱን ችግር ውስጥ እየከተተ እንደሆነ ይሰማዋል።

" እና እዚህ ቤት ለምን መጣህ??" ጎረሞቴው ነበር።

"ለማወቅ።"

"በንግግር ብቻ፤ ሁሉንም ነገር ልታውቅ አትችልም ልጅ።የግድ ያን ነገር ሆነህ መገኝት ይገባሀል። ያንድን ሰው ችግር የምትረዳው እሱ ባለፈበት መንገድ ስላለፍክ ሳይሆን እሱን ስትሆን ነው።"

"እና?"


"እናማ የግድ ጎረሞቴ መሆን አለብኽ።"



"ከዛ ምልከታው ሲጠናቀቅ ወደ ሰውነት የምትመልሰኝ ከሆነ።"





"ይ_ሁ_ና_" የተንኮል ፈገግታ ፊቱ ላይ እየተነበበ።