Get Mystery Box with random crypto!

ራት ቀረበ፤ ዓይብ ነበር የተመገቡት፤ የዓይቡ ጣዕም ግን ለየት ያለ ነበር፤ መድሐኒት መድሐኒት ይል | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ራት ቀረበ፤ ዓይብ ነበር የተመገቡት፤ የዓይቡ ጣዕም ግን ለየት ያለ ነበር፤ መድሐኒት መድሐኒት ይል ነበር። ወዲያው ዕንቅልፍ ወሰደው ፤ ከዕንቅልፉ ሲነቃ ከፊት ለፊቱ የሻማ ብርሀን ነበር።

"ትኩረት አድርግ።" የጎረሞቴው ድምፅ ነበር።

" አንድ ስለምታውቀው ሰው ፤ አስብ። በቀላሉ ስለ ሰካራሙ ተበጀ ፤ ለምሳሌ ነው ታድያ።" የጎረሞቴውን ድምፅ ተከትሎ የዮሮና አንጎል ይፈስ ጀመር።

በቀላሉ በሰካራሙ ተበጀ አዕምሮ ውስጥ ገብቶ ተሸጎጠ።

ተበጀ ምን ግዜም ጠጥቶ ወደ ቤቱ ስለሚመለስ፤ የሰፈሩ ሕፃናት ምን ጊዜም እንደተተናኮሉት ነው።

አንጎሉ ውስጥ ሆኖ ተበጀ ለምን መጠጥ እንደሚጠጣ አነበበ።

ሚስቱ ሌሊት ሌሊት የሚያስጮህ ዛር አለባት፤ እንዲሁ እንደጮኽች ዕንቅልፍ ባይኑ ሳይዞር ያድራል። የሚስቱ ሕመምና ዕንቅልፍ ማጣት ተባብረው ሊያሳብዱት ደረሱ። ከማበድ መስከር ይሻላል የሚል መላ አመጣ። የሌሊት ዕንቅልፉን የሚመልሱለት፤ ጭንቀቱን የሚያስረሱት፤ ሐዘንና ድባቴውን የሚረሳባቸው፤ መደበቂያዎቹ፤ መጠጦቹ፤ ሱሶቹ።

ከቀን ወደ ቀን ወደማይወጣው ሱስ እየገባ እንደሆነ ይታወቀዋል።


"ሚስቱን ግን ምን ያህል ቢወዳት ይሆን " ሲል አሰበ ዮሮና።

ሚስቱን በጣም ከመውደዱ የተነሳ እያያት ትናፍቀዋለች። የፈለገ ብታናድደው ብታሰቃየው ጧት ፊቱ ስትቆም ማታ ያሳለፈውን ስቃይ ሁሉ ይረሳዋል። ፊቷን በማየት ብቻ በውስጡ ይሰፍናል። አዕምሮው ረፍት ያገኛል። ዘላለም ፊቷ ተንበርክኮ ባያት፤ ባያትና ባመለካት እንኳን ሊፈታት ይቅርና።



ያለወትረው በጣም በማምሸቱና የሚሄድበት የገጠር ከተማ ራቅ በማለቱ፤ ሰካራሙ ተበጀ በአቅራቢያው ከምትገኝ ከተማ ገብቶ ለማደር ወሰነ።

ብር ስለጨረሰ ወደ አንዱ ቤት በረንዳ ተጠግቶ ተጋደመ።

።****

ዮሮና በ ሰካራሙ ተበጀ አዕምሮ ሆኖ፤ በተበጀ ጆሮ ያዳምጣል።

የተበጀን በረንዳ ላይ መተኛት ተከትሎ፤ የቤቱ መብራት በራ።

የሚጨቃጨቁ ባልና ሚስት ድምፅ ይሰማል።

በሩ ተከፍቶ ፤ ባል ወጣ፤ ሚስት ከባል ጀርባ

የተኛውን ሰካራም ቀሰቀሱት፤ ምስኪን ሰካራም


ቤቱ መኝታ የለው


ውጭም አባረሩ።

ቤቱ ካልተኛ


ደጅ ካልተኛ



የት ይተኛ??



ይቀጥላል

For more https://t.me/hiyawnet