Get Mystery Box with random crypto!

በአንድ ወቅት ስለ ባለ ዕፀ-መሰውሩ ተማሪ በስፋት ይወራ ነበር፤ ግቢው ውስጥ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

በአንድ ወቅት ስለ ባለ ዕፀ-መሰውሩ ተማሪ በስፋት ይወራ ነበር፤ ግቢው ውስጥ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር አንድ ሰሞን።

ተሰውሮ ሴቶች ዶርም ስለሚገባው፤ ተሰውሮ ካፌ ገብቶ ስለሚመገበው ተማሪ።

ተሰውሮ መምህራን ቢሮ ገብቶ ፈተና የሚሰርቀው፤ የሚወዳትን ልጅ ሻወር ስትወስድ ክፍሏ ገብቶ የሚሻፍደው ተማሪ።

ተሰውሮ የተማሪዎትን ታብሌትና ላፕቶፕ የሚሰርቀው ተማሪ።


አንድ ቀን፥ ሳያስበው ኤሌክትሪክ ያዘውና ተዝለፍልፎ ወደቀ።

ሆስፒታል በሄደና በታከመ፤ በዳነም ነበር።

ምንም ዋጋ አለው ፤ አይታይምና የሚረዳው ሰው አላገኘም።

****።



ዮሮና የልጁን ታሪክ እንዳነበበ ፈገግ አለ።

" ሕይወት እንደዚል ናት፤ አንዳንድ ሰዎች ፀጋቸው መጥፊያቸው ይሆናል። ገንዘባቸው፤ ዝናቸው፤ስልጣናቸው፤ ዕውቀታቸው ፤ ተስጥዖዋቸው መጥፊያቸው የሆኑ ሰዎች አሉ።" ሲል አሰበ።




ይቀጥላል