Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ...ሆሳዕና ነገ ሆሳዕና ምን ያደርግና ሰላም የለምና ፍቅር የለምና ብዬ ሳልጨርስ በገና ክር | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ዛሬ...ሆሳዕና
ነገ ሆሳዕና
ምን ያደርግና
ሰላም የለምና
ፍቅር የለምና
ብዬ ሳልጨርስ በገና

ክርስቶስ በአህያይቱ በጉዝጓዝ መምጣቱ
ዛሬን ሊያሳይ ይሆንን እውነቱ፣

ነገ ላይ
ያቺ አህያ ሰላም ጭና፣
ስጋውን ረግጣ ክርስቶስ ሁና
ታምጣልን በጉዝጓዝ በ'ለተ ሆሳዕና

ነገ
ሰላም ሆኖ ታዬኝ ደዋዊው ሲነጣ፣
ታየች አህያይቱ በእውን ስትመጣ፣
ቄጤማ ግጫው ለፍቅር ሲዋጣ፣

ይታዬኛል ግጫ በራሳችን አስረን፣
ይታዬኛል ሰላም
በገዛ እረፍታችን ነፍሳችን ጋብዘን ፣

ይታዬኛል ጉዝጓዝ ይታዬኛል ሲራዝ፣
እንደ ሰለሜ ባሪያ ብርቱ ሰላም ሲጋዝ፣

ፍቅር ባሪያ አርጎን ሲበተን ጉዝጓዝ
ታዬኝ ጥላቻ  በበርሃ ሲጋዝ..

ይታዬኛል....


___ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat