Get Mystery Box with random crypto!

የዶርም ጓደኞቹ በሙሉ ወደ ክፍል ሄደዋል። ታሞ ክላስ መቅጣት ከጀመረ ሳምንት ሊሆነው ነው። ወደ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የዶርም ጓደኞቹ በሙሉ ወደ ክፍል ሄደዋል።

ታሞ ክላስ መቅጣት ከጀመረ ሳምንት ሊሆነው ነው።

ወደ ሞት የተቃረበ ይመስለዋል፤ የልጅነት ትውስታዎቹ ያላንዳች መደብዘዝ ቅርብጭ ብለው ይታዩት ጀምሯል።

ከልጅነት ጓደኞቹ ጋር ውሀ ላይ ለ ሶስት ሆነው ሲሸኑ፤ ገጠር እያሉ አጎዛ አንጥፈው ሲተኙ፤ በሌሊት የጅብ ጩኽት፤ አልጋ ላይ ሸንቶ አያቱ የቆነጠጡት።

ትውስታዎቹ ምስል ፈጥረው ፤ አጠገቡ ሆነው ታዩት።

በየቀኑ ሕመሙ እየባሰበት ሲሄድ ይሰማዋል።