Get Mystery Box with random crypto!

ዮሮና ቤተ መጻሕፍት ገብቶ ለነገው ፈተና እያነበበ ነበር። ድንገት ስልኩ ኖቲፊኬሽን አመጣለት። በ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ዮሮና ቤተ መጻሕፍት ገብቶ ለነገው ፈተና እያነበበ ነበር።

ድንገት ስልኩ ኖቲፊኬሽን አመጣለት። በቴሌቪዥን የሚታይ አስቂኝ ሲትኮም ነበር፤ በአንድ ደስተኛ ቤተሰብ ዙርያ የሚያጠነጥን ነበር ታሪኩ።

ሚስት ባልን ከተኛበት ትቀሰቅሰዋለች፤ ባል ከ ዕንቅልፉ እየተነጫነጨ ተነሳ፤

ሚስት፡ በረንዳው ላይ የተኛ ሰው አለ

ባል፡ ማን አባቱ ነው? ( እንደፈራ ሁኔታው ይናገራል፤ እንዳልፈራም ለማስመሰል ይጥራል።)

ሚስት፡ ፈራህ እንዴ??

ባል፡ ምን ያስፈራኛል?( ቆጣ ብሎ)

በሩ ላይ ባል እየተንጎራደደ ይሁን እየተወላገደ ባለየለት ፤ ቅጥ ያጣ እንቅስቃሴ ያካሂዳል።

ዮሮና ሲትኮሙ እስኪያልቅ በፈገግታ ነበር ሲከታተል የቆየው ።

ቤተሰብ ቢኖረኝ ሲል ተመኘ፤ ቤተሰብ ቢኖረው እንዴት ደስተኛ ሊሆን እንደሚችል አሰበ።