Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል ምናምን ዮሮና ከዕንቅልፉ ሲነቃ፤ ነጭናጫ ሚስቱን አጠገቡ ቆማ አገኛት። ዓይኖቹን ለመግለጥ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ክፍል ምናምን

ዮሮና ከዕንቅልፉ ሲነቃ፤ ነጭናጫ ሚስቱን አጠገቡ ቆማ አገኛት። ዓይኖቹን ለመግለጥ እየታገለ፤ ለመነሳት ሲሞክር ሀያሉ ዕንቅልፍ በኩርኩም ብሎ አጋደመው።

ሚስት በንዴት አንሶላውን ከ ላዩ ላይ ገፈፈች፤ ድንብርብር እያለ ከዕንቅልፉ ተነሳ።

"በራችን ላይ ሌባ ተኝቷል ፤ አንተ እዚ ተጋድመህልኛል። ጋድሚያም።" ወገቧን ይዛ እየተውረገረገች ነበር የተናገረችው።

" ሌባ በዚህ ሰዓት ምን ያስተኛዋል፤ ወደ ስራው ይሰማራል እንጂ። " አለ በሩን ከፍቶ ቢወጣ የውጭውን ቅዝቃዜ ሲያስበው እየዘገነነው።

"እና እኛ በር ላይ ነው የሚተኛው?? በራችን ሲደፈር ዝም እንበል??" ሚስት በገነች።

* ****

" በራችን ሲደፈር ዝም እንበል??" አሁን አንድ ነገር ቢፈጠር የምታግዝ አትመስልም?? ወይኔ ዮሮና የማንም አሮጊት መጫወቻ ልሁን??

"ሴትዮ በዚህ ብርድ አልወጣም" እንደ አባወራነቴ ቆጣ ብዬ።

"ሊቆጡም ያምሮዎታል?? ድሮስ የርስዎ አምባገነንነት በኛ ላይ ነው እንጂ ።"

ኡፍ አሽሙሯን ጀመረችኝ። ቀጥታ ቢናገሩ ጥፊ እንቀምሳለንን የፈሩ ሚስቶች ማጥቂያ፤ አሽሙር።

የሚፈልጉት ነገር ካልተደረ፤ ቀኑን ማጉረምረም፤ማማረር መነጫነጭ።

ንጭንጭን እንደ ጦር መሣሪያ መጠቀም፤

ሁፍ ምነው ባለትዳር ባልሆንኩ፤ መች ቀን ነው ያገባሁት ብሎ ማማረር፤ ሲያገቡ እንዳልተደሰቱ፤ የፍቅር ጥያቄያቸው ምላሽ ሲያገኝ እንዳልፈነጠዙ።


*
ቀና ሲል ዕንቅልፍ ወስዶት እንደነበር ተረዳ፤ የላይብረሪ ተቆጣጣሪው ነበር ከ ዕንቅልፉ የቀሰቀሰው።