Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitmnamuzika — ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹
የሰርጥ አድራሻ: @gitmnamuzika
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.30K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብበት ቻናል ነው ይከታተሉ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ ሚክስ ከፌሊኖቫ ጋር
Creator@fellynovaa
Invite link to share
https://t.me/ vKDN0lXKiKFmN2M0

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-22 00:48:52
የገጣሚ ግዕዝ ሙላት የ YOUTUBE ቻናል







subscribe pls
@geez_mulat on telegram
211 viewsጥ ቁር ዝምታ, edited  21:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 19:08:26 ጥያቄ?
ልብ ስጋ ነው ወይ ነፍስ ??
____
ተይ በታቦቱ
ተይ በሰማእቱ
ተይ በአርባራቱ

ላስይዝሽ እባክሽ በእናትዋ ባታ
በተወለድሽባት በቅብአ ቦታ

ታቦት ብዘረዝር ጎንደሬ አረጉኝ
አድባር ብጠራ ጎጃሜ ነህ አሉኝ

ይቆጠራል እንዴ ታቦት በአንድ አድባር
እምነት ለዓለም ነው ማን ሰጠው ለምድር

ጥያቄ ?

ታቦትን ለጎንደር የሰጠውስ ማነው
አባይን ለጎጃም የሰጠውስ ማነው
የኔን ልብ ላንቺ የሰጠውስ ማነው
እንደው አትፍረጂ ያው ያንቺ አምላክ ነው
ወንድ አዳም ልቤን፥ በሔዋን ሚያመልከው
ያፈቀረ ንፉግ እግዜር ከየት ሊያቀው?

መልስ ?

ታቦቱን ማንሳቴ
ጠበሉን ማንሳቴ
እንድትመጭ ነበር ያስያዝኩሽ በእምነቴ

እምነቴ አልበጀኝ ለልቤ ባረዳ
ነፍስ አፀድቅ ተብሎ ስጋ ለሚጎዳ

ምንድነው መልሱ?

ጥያቄ እኮ አለኝ ወትሮም ሰለስት ላሳዬ፣
ሰው ልብ ይላሉ አድባሩን ላዋዬ

ልብ ግን ስጋ ነው?
ከስጋ ተርታ ነውስ ሚመደበው?
ወይስ
ከነፍስስ ነው?
በእግዜር ዘንድ በሰማይ ሚታዬው ?

እና
የስጋ ከሆነስ ለፅድቅ ይሆናል?
አንቺን ማፍቀሬ ለነፍስስ ይባላል?

መልሽልኝ ????

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
578 viewsጥ ቁር ዝምታ, 16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 22:07:33 ደህና ነበርኩ እኮ

ሳልወድሽ በፊት ገና ልቤ ሳትነግሽ
በአይኔ ሳትዞሪ እንደውሃ ሳትፈሽ፣

እንደልጅ ጨርቅ ኳስ አይኔ ሲንከባለል፣
ያላወቀ መስሎ በአንቺው ሳይደለል

መርሳት ራሱ ራሴን ሳይረሳው
የሸጥኩት ደስታዬ በውድ ሳለምነው

ፊቴ ወዝ ሳያጣ  ትዝታ ሳይተካ
አይኔ ሳያብጥ የእንባ ውሃ ሳይነካ

ፀጉሬ ሳይጨበርር ቅባት ሳያጣው
ከንፈሬ ሳይደርቅ ድርቅ ሳይመታው
አይኔ ውሃ ሳያጣ ትዝታሽ ሳይሞላው
የድሮ መልኬን ጎረቤት ሳይጠላው

ያኔ ገና ሳልወድሽ በነበርኩ
ማሪያምን ነው ምልሽ እኔ ደና ነበርኩ


@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
743 viewsጥ ቁር ዝምታ, 19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 19:21:57 ተስፋን በህልም ፈራሁ

ፈራሁ እንዳላጣሽ ፈራሁ
ትናንትናም ዛሬም
የማይሆን ህልም አለምሁ
ፈራሁ ...
የመኖሬን ምክንያትአንች ላይ ስላጣሁ
ፈራሁ
ፈራሁ
ህልሜ ተደገመ
አዲስ ህልም ለማለም ቀድሜ በተኛሁ
ፈራሁ
ፈራሁ
ህልሜ ሊበተን ነው የማይሆን ህልም አየሁ
ፈራሁ
የኔ ፍቅር ፈራሁ
አንችን በማለቴ
ከሁለቴ በላይ በህልሜ ተቀጣሁ
ፈራሁ
ፈራሁ
ላገኝሽ ብተኛ ክፉ ቃልሽን ሰማሁ
እናም
ፈራሁ... ነገን ማለም ፈራሁ
ፈራሁ...መተኛትን ፈራሁ
ፈራሁ... መኖርንም ፈራሁ
እንዴት ብየ
ልድፈር የጠቆረ ፊትሽን በህልሜ እያየሁ
ስለዚህ የኔ ውድ
ባንች ተመርኩዤ መኖር እንዳጣጥም
እድሌ ከእድልሽ በልኩ እንዲገጥም
ፈገግ በይ ና ነይ
የሌሊቱ ህልሜ በደስታ ይፈጠም
by belaya

https://t.me/poem_by_poem
914 viewsbelaya, 16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 19:09:38
ለ አንድ ሳምንት ተራዝሟል


የተወደዳችሁ ተገጣሚዎች

ይህ ዕድል እንዳያመልጣችሁ

ቲኬቱን የምትፈልጉ @yaviye
858 viewsያቢ ነኝ, 16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 21:20:29 ለባሉ
_
ፊዬሪ ነሽ የጮራ
የልብ ነሽ የአስመራ?

የነፍስ ነሽ የ ማክተሚያ
የዘመን ነሽ የማደሪያ

የባሉ ጦር ማዕረግ
የብዕሩ  የዘር ሀረግ
የግርማ ልጅ የሴቱ ደግ

ፊዬሪዋ ግዕዝነት
ዴዴብዋ አስመራነት !
የጦርዋ አዋቂነት
አምሳልዋ የደግነት
አምሳሊቷ የእንባነት፣
አባቴ ሙት ላለች ገዳይ ፈጣሚነት፣
---
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat

መታሰቢያነቱ

ለደራሲ በዓሉ ግርማ
143 viewsጥ ቁር ዝምታ, 18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 21:57:48 ከጨለማ ያውጣን ከሞት ቤቱ አዳር
ተነሱ ይበለን መጥቶ እንደአላአዛር

ድምፆችን ይስማን እንደመቅደላዊት፣
በግንቡ ይጎብኜን መጥቶ በኛ ሌሊት፣

እንደመሼ መስሎ የፍሲካ ማታ
አጋጣሚ አይደለም ሳይፀና ወገግታ
በ ዘጠኝ ሰአቱ የተነሳ ጌታ

ሊያመስለን ቢሻ ነው የኛኑ ወገግ ማለት
ፀሀይ ሳትወጣ ሌቱ ሳይነጋበት

ክርስቶስ ሌባ ነው በሌሊት ይመጣል
ክርስቶስ ሊዘርፈን በሌቱ ይገኛል

ሀር ነጩን ለብሶ ሌሊት ሳይታዬን
ጉዝጓዝ መከራችን ሳይታይ ሊሰርቀን
ሰርቆ ጠራርጎ ፍቅር ሊያበድረን

ፍቅር ሊተካብን በልባችን ሳንቃ፣
ክርስቶስ ይሰርቃል
ሊነጋጋ ሲል እንባን እና ሲቃ፣
__

ይነጋል ሲነቃ ይነጋል

# አይዞን ፍሲካችን አለ #


# ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat
1.2K viewsጥ ቁር ዝምታ, 18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 18:38:14 ዮሮና የተወለደው በ አርባምንጭ ከተማ ሲሆን፤

የ አንደኛ ደረጃ ትምህርቱን ናዓው ጊሽን(በሁለት ሲካፈል) ሄዛው ጊሽን (በሶስት ሲካፈል) ዕያለ ሂሳብን በ ጋሙኛ ቋንቋ ተማረ።


ወዘተ




ወዘተ



ካላልን የማይገባቹ አንባብያንን አስተውለናል።


ቀስ ዕያለ የአፃፃፍ መንገዳችንን እንደምትለምዱት ተስፋ እናደርጋለን።

በ ጋሞ ውስጥ ሶስት ዓይነት ማህበረሰብ አለ።

ሰዎች



መናዎች


ጎረሞቴዎች



መናዎች ብዙን ጊዜ ፀሐይ በደመናዎች ሳትከለል ከዘነበ ሚስት ያገባሉ ተብሎ ይታሰባል። የስራ ዘርፋቸው ሸክላ ሰሪና ብረት ቀጥቃጭ ናቸው።



ጎረሞቴዎች ብዙን ግዜ ከሰው አይቀላቀሉም።


ለብቻቸው ጫካ ውስጥ መኖር ያዘወትራሉ።


አልፎ አልፎ አንዳንዶች ከሰዎች ጋር ተመሳስለው ይኖራሉ።


ርስበርስ በጢንዚዛ መልዕክት ይለዋወጣሉ ተብሎ ይታሰባል።


አልፎ አልፎ ከሰው ልጆች ጋር በመጋባት አዲስ ዝርያን ይፈጥራሉ። ነገር ግን ከ ጎረሞቴ ጋር የተጋባ ማንኛውም ሰው ከፍተኛ የሆነ መገለል ይደርስበታል።
581 viewsያቢ ነኝ, 15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 15:33:10 እንኳን መታውህ ጅራፍ ሰነዘርኩ


ግዕዝ ሙላት

@geez_mulat
@geez_mulat
158 viewsጥ ቁር ዝምታ, 12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 17:49:49 ክርስቶስ ሞኝ ነው ?

ክርስቶስ ግን ሞኝ ነህ
ድጋም ልበድልህ
ድጋም ላሰቅልህ
ድጋም ላስገርፍህ
ለእኔ ለማረባው ለምን ትለፍለህ?
አዳም ብልጥ ሁኗል ለምን ትሞኛለህ?

ሰቅየህ ላይበቃህ ጭራሽ መግረፌ
አዳምን ስመስል በአንተ ዘንድ መትረፌ

እንኳን መታውህ ጅራፍ ሰነዘርኩ፣
ያኔ ባትምረኝ እኔን ባልነበርኩ፣


የጀርባህ መስመር ላይ የመስመሩ ጅማት
ፍቅርን ነው የሳለ ወይስ ዙፍን ጥማት
እያለ ሲጠይቅ በደምህ ላይ ክፍት

አዳምም ሞኝ ነው ሴጣንን ይወዳል
ፍቅርን እየገፍ ፍቅር ላይ ይተርፍል

እንደው ባምን እጂ በምን ለምመካ
የወገብህ ስፍት ስንት ግፍን ለካ
የሔዋን እንባ ነው? በደምህ ምትለካ
ያዳምን አጥም ነው በስጋህ ምትለካ

አምላክ ሆይ ንገረኝ ከበትርህ ወርደህ
ሰውነትክን ከፍለህ በደምህ አስታጥበህ
ላተረፍከው አዳም አንተ ሙሴው ነህ ?
ወይ? ከእርሱ ትበልጣለህ?

ቀድሶ ማይፀና መርምሮ ይደክማል፣
ስጋ መከፈሉ ከውሃ እንዴት ይለካል፣
ዓለምን ማትረፍ ከእስራኤል ይደርሳል?
ሙሴን ለፈጠረው ከአምላኩስ ይበልጣል?

(አዳም ሞኝ )

ስጋህ እስኪያምህ በስጋ ተመተህ፣
ደምህ ትን እስኪልህ በጫፉ ተወግተህ፣

ለማን ይሆን ዋጋው ሰው እኮ ሞኝ ነው
አንተን እየረሱ ሙሴን ነው ሚያነግሰው?
አሁን አላየህም እጂ ሰው እኮ ጌታ ነው !

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
468 viewsጥ ቁር ዝምታ, 14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ