Get Mystery Box with random crypto!

ተስፋን በህልም ፈራሁ ፈራሁ እንዳላጣሽ ፈራሁ ትናንትናም ዛሬም | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

ተስፋን በህልም ፈራሁ

ፈራሁ እንዳላጣሽ ፈራሁ
ትናንትናም ዛሬም
የማይሆን ህልም አለምሁ
ፈራሁ ...
የመኖሬን ምክንያትአንች ላይ ስላጣሁ
ፈራሁ
ፈራሁ
ህልሜ ተደገመ
አዲስ ህልም ለማለም ቀድሜ በተኛሁ
ፈራሁ
ፈራሁ
ህልሜ ሊበተን ነው የማይሆን ህልም አየሁ
ፈራሁ
የኔ ፍቅር ፈራሁ
አንችን በማለቴ
ከሁለቴ በላይ በህልሜ ተቀጣሁ
ፈራሁ
ፈራሁ
ላገኝሽ ብተኛ ክፉ ቃልሽን ሰማሁ
እናም
ፈራሁ... ነገን ማለም ፈራሁ
ፈራሁ...መተኛትን ፈራሁ
ፈራሁ... መኖርንም ፈራሁ
እንዴት ብየ
ልድፈር የጠቆረ ፊትሽን በህልሜ እያየሁ
ስለዚህ የኔ ውድ
ባንች ተመርኩዤ መኖር እንዳጣጥም
እድሌ ከእድልሽ በልኩ እንዲገጥም
ፈገግ በይ ና ነይ
የሌሊቱ ህልሜ በደስታ ይፈጠም
by belaya

https://t.me/poem_by_poem